ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፯ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ሰባተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

ልዑል እግዚአብሔር፡
እንኳን፡ ለ፳፻፯ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ሰባተኛው)
ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡
በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡
ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

+ + +

መግቢያ

እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥና በመላው ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ ይህን ከመሰለው የጾምና ጸሎት ሱባዔያችን የተነሣ፡ እነሆ፡ ከዚሁ ጊዜ ለመድረስ አብቅቶናል፤ ስለዚህ፡ ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምሕላ ጸሎታችን፡ ልንፈጽማት ይገባናል።

ይኸው ጾማችንና ጸሎታችን፥ ምሕላችንና ሱባዔያችን፡ ከዚህ በፊት፡ ለ"ጾመ ኢትዮጵያ፡ ተዘጋጅቶልን የተገለገልንበትን፡ ያንኑ ሥርዓትና መመሪያ የተከተለ ይኾናል። ይህንም፡ የ"ጾመ ኢትዮጵያ"ን፡ የጾምና የጸሎት፥ የምሕላና የሱባዔ ሥርዓትና መመሪያ፡ በዚሁ የኅዋ ሰሌዳ ላይ፡ "ቤተ መዛግብት" በሚለው ክፍል ውስጥ፡ እናገኘዋለንና፡ ያን ከፍተን፡ በመመልከት፥ ዐትመንም በማውጣት፡ ልንጠቀምበት ይቻለናል።

ሙሉውን ንባብ ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ! ...

ሥርዓተ ጸሎት፦

የሥርዓተ ጸሎቱ ዜማ፦

https://soundcloud.com/ethkogserv/orpyehtjm76o