Messages
በመላው ዓለም ለሰፈነችው ኢትዮጵያና |
ልዑል እግዚአብሔር፡ የ፯ሺ፭፻፯ (የሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባተ)ኛውን ዓመት፡ የ፪ሺ፯ (የኹለት ሺህ ሰባተ)ኛውን ዓመት፡ ለአዲሱ የ፪ሺ፯ (፳፻፯) |
መስከረም አንድ ቀን፡ በርእሰ ዓውደ ዓመት፥ |
ልዑል እግዚአብሔር፡ |
ዮም ፍሥሓ ኮነ! በእንተ ርደተ መንፈስ ቅዱስ፡ ላዕለ ሓዋርያት፡ በጽርሓ ጽዮን ቅድስት! ይድረስ፦ ለኪዳናውያንና ለኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች! በያላችሁበት! ከኪዳናዊ ወንድማችሁ፡ ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ እና ከኪዳናዊት እኅታችሁ፡ ከእመቤት ራሔል ዘካርያስ። የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያ አገልጋዮች። "እንደምን አላችሁ?" እያልን፡ ኪዳናዊ የኾነ፡ ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን። እግዚአብሔር ይመስገን፡ በቅድስት እናቱ፡ ድንግል ማርያም፡ ረድኤትና በረከት፡ እኛ ደህና ነን። |
ተፈጸመ ትስብእት፡ በኢትዮጵያ ማርያም ድንግል! ይድረስ፡ ለኪዳናውያት እና ለኪዳናውያን፡ "የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ልጆች"፥ እኅቶቼና ወንድሞቼ፥ የክህነት ባልደረቦቼም! በሰማያቱ የዘለዓለም አባታችንና እናታችን ስም፡ ከነቤተሰባችሁ፡ በያላችሁበት፡ "እንዴት አላችሁ!" እያልሁ፡ ኪዳናዊና ኢትዮጵያዊ ሰላምታዬን፡ አቀርብላችኋለሁ። ለእነርሱ፡ ምስጋናችን ይድረሳቸውና፡ ዐብረውኝ ካሉት ጋር፡ እኔ ደኅና ነኝ። |
የጾመ ኢትዮጵያ (ነነዌ) መልእክትና ሥርዓተ ጸሎት። በስመ እግዚአብሔር አብ፥ ወወልድ፥ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ፤ “ጾመ ኢትዮጵያ” |
በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት |
የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ሆሣዕና እና |
ፈጣሪያችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት፡ በዜማ! |
ዮም ፍሥሓ ኮነ! ዛሬና እንግዴህ ወዲህ፡ ደስታ ኾነ! + + + ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ በባዕዳን ዘንድ፡ "የአባቶች ቀን" እና "የእናቶች ቀን" እየተባሉ |
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ለቅዱሱ ኪዳን ሕያውና መለኮታዊ ስለኾነው፡ የግእዝ ቋንቋችንና የፊደል ገበታችን፡ እግዚአብሔር፡ በኢትዮጵያውያኑና በኢትዮጵያውያቱ ሕፃናት፥ በሞግዚት ወላጆቻቸውም መሣሪያነት፡ የፈጸመውን፡ ዕፁብና ድንቅ ተኣምራት፡ በመንፈሳዊ አትኵሮትና ተመሥጦ ኾናችሁ ትከታተሉት ዘንድ፥ ደግሞ፡ እናንተም፡ እያንዳንዳችሁ፡ ራሳችሁን፡ ለዚህ፡ የተቀደሰ በረከት፡ ታበቁ ዘንድ፡ ይኸው፡ የተኣምራቱን፡ የምሥራችና የትፍሥሕት ዜና፡ እንደሚከተለው አዘጋጅተን አቅርበንላችኋል። |
ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ተደብቀው የኖሩ፡ አዳዲስ ምሥጢራትን የገለጠችባቸው፣ ከዮሓንስ ኢትዮጲስ ለቀረቡ፡ አብርሆትና አርትዖት፡ በኪዳናዊ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ (ንቡረ-እድ) + + + ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፩ደኛ ጥያቄ፡- ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾኑ፡ ማረጋገጫዎ ምን እንደኾነ ልጠይቅዎ ግድ ይለኛል? የትኛው መጽሓፍ ቅዱስ፡ ይህን ይናገራል? ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ከኾነ፣ "የጥንቶቹ አይሁድ፡ ከኢትዮጵያውያን ጋር፡ በአካል ተመሳሳይ ነበሩ፤" ማለት ነው? ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡- |
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት። ይድረስ፦ ለቅዱሱ ኪዳን፡ "የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያዋ ድንግል ማርያም ልጆች!" እየራሳችሁን፡ ለዚህ ታላቅ ኪዳናዊ ጸጋ እንደምታበቁ ለታመነባችሁ፡ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ርእሰ ብሔር፡ + + + በእግዚአብሔር አብወእም፥ ወወልድ፥ ወመንፈስ ቅዱስ ስም፡ የ"ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት" |
ልዑል እግዚአብሔር፡ + + + መግቢያ እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥና በመላው ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ ይህን ከመሰለው የጾምና ጸሎት ሱባዔያችን የተነሣ፡ እነሆ፡ ከዚሁ ጊዜ ለመድረስ አብቅቶናል፤ ስለዚህ፡ ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምሕላ ጸሎታችን፡ ልንፈጽማት ይገባናል። |
እግዚአብሔር አብወእም፡ + + + የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል። |
አግሃደት ፍልሰታሃ፡ ማርያም ድንግል! ድንግል ማርያም፡ ፍልሰቷን ገለጠች! + + + ልዑል እግዚአብሔር፡ + + + ፍልሰታሃ ለማርያም! ድንግል ማርያም፡ ሰማያዊ ልዕልና፡ ዘበዓለ ፍልሰታ ለማርያም። |
"ጾመ ጳጉሜ" እኛ፡ የቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፡ "ጾመ ፍልሰታ" ካበቃች በኋላ፡ ኹለት ሳምንቶችን፡ በሥጋዊውና በመንፈሳዊው የፋሲካ ደስታና የሓሤት ድግሥ ቆይተን፡ "ጾመ ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "የጳጉሜ ጾም" ብለን፡ ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከል፡ አንዲቱ ኾና የምታስተናግደን፡ ትንሿ ሰሞን ትቀበለናለች። እርሷም፡ በመስከረም ፩ ቀን ለሚውለው፡ ለታላቁ የዐውደ ዓመት በዓላችን፡ ሰሙነ ዋዜማ የኾነችው፡ የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን ናት። "ጳጉሜ" ምን ማለት ነው? |
መስከረም አንድ ቀን፡ በርእስ ዓውደ ዓመት፥ መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!... |
ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ሉቃስ ወደዘመነ ዮሓንስ አሸጋግሮ፡ የ፯ሺ፭፻፰ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ስምንት)ኛውን ዓመት፡ የነጻነት ሕልውናችንን በዓል፥ ይልቁንም፡ የእግዚአብሔር እም ድንግል ማርያምን፡ የ፪ሺ፳፬ (የኹለት ሽህ ሃያ አራት)ኛውን ዓመት፡ እና የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስን፡ የ፪ሺ፰ (የኹለት ሽህ ስምንት)ኛውን ዓመት፡ የልደታት በዓል ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ የ፪ሺ፰ (፳፻፰) (ኹለት ሺህ ስምንት፥ ወይም ሃያ መቶ ስምንት፥ ወይም፡ ዕሥራ ምዕት ወሰምንቱ) ዓመተ ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣ ደግሞም፡ ለፍጥረተ-ዓለሙ ባለው ፍጹም ፍቅሩ፡ በተቃዋሚው የክፋት ኃይል ፊት፡ እንደበግ ተሠውቶ፥ እንደአንበሳ፡ በድል አድራጊነት የተነሣው፡ የቤዛችን፡ የኢየሱስ መሢህ፡ የግዝረቱ፥ የዕፀ መስቀሉና የደመራው፥ የበዓተ መቅደሱና የስደቱ በዓላት፥ ከእነዚህም ጋር ተያይዞ ለሚደርሰው፡ የፍጥረተ ዓለሙ መድኃኒትና እናት ለኾነችው፡ ለቅድስት ድንግል ማርያም፡ የፍልሰተ ዕርገቷ በዓል፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በሰላም አደረሰን! |
በቅዱሱ ኪዳን ፍቅር፡ ሰላምታችን፡ በያላችሁበት ይድረሳችሁ እያልን፦ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ "ነገላ" በተባለች፡ በአንዲት የሰሜን ኢትዮጵያ ወረዳ፡ ከእርሱ ጋር፡ ሰባት ሰበካዎችን ባካተተው፡ "ሓዋርያት አቦ" በተባለው ቀበሌ ውስጥ ከሚኖሩና ከልጆቿ መካከል፡ "የተለየ ዝና አላቸው!" ከሚባሉ ወገኖች ጋር፡ እያደረገች ያለውን፡ የአገልግሎት ግንኙነት የሚገልጹ ጽሑፎችን፡ ትመለከቷቸው ዘንድ፡ እንደሚከተለው አሰናድተን አቅርበንላችኋልና፡ መልእክቶቹን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ ከታች የተመለከቱትን፡ የእያንዳንዱን፡ የመገናኛ ቍልፍ በመጫን፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...
|
ልዑል እግዚአብሔር፡ የዛሬ ኹለት ሺህ ስምንት ዓመት፡ በታኅሣሥ አንድ ቀን፡ ባለሟሉን መልአክ፡ ቅዱስ ገብርኤልን፡ ወደቅድስቲቱ ኢትዮጵያዊት ድንግል ማርያም ልኮ፡ “ወናሁ ትፀንሲ! ወትወልዲ ወልደ! ወትሰምይዩ ስሞ ኢየሱስ!” ማለትም፡ “እንሆ ትፀንሻለሽ! ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ! ስሙንም፡ ‘ኢየሱስ’ ትይዋለሽ!” ሲል በተናገረው አምላካዊ ቃሉ፡ “ታላቁን፡ መለኮታዊና ዘለዓለማዊ ምሥራች!” ለፍጥረት ዓለሙ ላሰማበት፡ ለዚች፡ ለ፪ሺ፰ (፳፻፰)ተኛው የጌታችን ኢየሱስ መሢሕ በዓለ ትስብእት፡ (የፅንሰቱና የብሥራተ ገብርኤል በዓል) እና ታኅሣሥ ፯ ቀን ለሚውለው ለቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰቷ በዓል፡ በያለንበት፡ እንኳን አደረሰን! መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ዮም ፍሥሓ ኮነ! ዛሬ፡ ደስታ ኾነ! |
ዮም ፍሥሓ ኮነ! ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት። ይድረስ፦ ለተከበራችሁትና ለተወደዳችሁት አንባቢዎቻችን! በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን፡ በነፍስ፥ በሥጋና በመንፈስ፡ ልጆቹና ነጋሢዎቹ፥ ዜጎቹና አገልጋዮቹ ባደረገን፥ በዘለዓለሙ ህልውናችንም፡ ሕያው አባታችንና እናታችን፥ ወንድማችንና እኅታችን፥ ጓደኛችንና ሕይወታችን በኾነው፡ በቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ስም፡ ኪዳናዊዉን ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን፡ በያላችሁበት እናቀርብላችኋለን። |
ፈጣሪያችንና አምላካችን ኢየሱስ መሲሕ፡ ከማትለየው፡ ቅድስት እናቱና እናታችን ድንግል ማርያም ጋር፡ አስቀድሞ፡ ጾመ-ኢትዮጵያን፥ አከታትሎም፡ ዓቢይ-ጾምን አስፈጽሞ፡ ለዘንድሮው በዓለ-ሆሣዕናና ሰሙነ ሕማማት፡ እንኳን፡ በደኅና አደረሰን! የ፪ሺ፰ ዓመተ ምሕረት የሕማማት መልእክትና ሥርዓተ ጸሎት። ይድረስ፡- በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፥ ነጋሢዎች እና ካህናት (የአገልግሎት ባልደረቦች)፥ ዜጎችም ኾናችሁ፡ “ኢትዮጵያ” በተባለችው አገር ሠፍራችሁ፥ በዓለሙ አህጉራትም ተዘርታችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ "የቅዱስ ኪዳኗ ኢትዮጵያ ልጆች!" ለኾናችሁት ወገኖቻችን! በእግዚአብሔርና በቅድስት እናቱ ድንግል ማርያም ስም፡ ኢትዮጵያዊውን ሰላምታችንን፡ በያላችሁበት እናቀርብላችኋለን። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፰ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ስምንተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን! + + + መግቢያ እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው! |
የ፳፻፰ ዓ.ም. የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል መልእክት። + + + የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ |
የእግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት። ከመስከረም ፩ ቀን፡ የርእሰ ዐውደ-ዓመት በዓል ጋር፡ ዐብሮ ስለሚታሰበው፡ ስለእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ የልደቷ በዓል፡ እዚህ ላይ፡ ሊታወስ የሚገባው ቍም-ነገር አለ። ያንንም፡ እንደሚከተለው ገላልጠን አቅርበንላችኋል፦ መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
በያለንበት፡ በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፥ የምትጠብቀንንና የምትመራንን፡ ቸሪቱን ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያመሰገንን፥ "እንኳን ለጾመ-ነቢያት ሥርዓተ-ሕይወታችን ቅበላ አደረሰንም!" እያልን፥ በሰማዩ አባታችንና በሰማይዋ እናታችን ቅዱስ ስም፡ የተከበረ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን። የ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መንፈስ ቅዱሳዊ መልእክት፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋልና በተለመደው የጥሞና መንፈስ ኹናችሁ ተከተታተሉት። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ በኢትዮጵያዊው ሥርዓት፡ ጥር ፩ ቀን ለሚከበረው፡ ለ፳፻፱ (፪ሺ፱)ኛው ዓመት የሰላማችን የኢየሱስ መሲሕ ጥምቀት፣ እንዲሁም፡ ለተአምራዊው የቃና ዘገሊላ ሠርግ፥ ለመድኃኒታችን ድንግል-ማርያም ሰማያዊ ፍልሰትና ለኪዳነ ምሕረት በዓላት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅንነትና በሰላም አደረሰን! የእናቲቱ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም እና የልጇ የወዳጇ የእግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕ በዓላተ-ትስብእት፡ በእርሱ፡ በታኅሣሥ ፩ዱ ቀን ተጀምሮ፡ በእርሷው፡ በታኅሣሥ ፯ቱ ቀን በኩልም ዐልፎ፣ የረቡዕና የዓርብ ጾምም እንኳ ሳይኖርበት፡ በፍጹሙ የጾመ-ማርያምነት መንፈሳዊ ደረጃ እየተካኼደ፡ "ከተራ" እስከሚባለው፣ በአንዲት ቀን የጋድ ጾም እስከሚዘከረው፡ እስከጥምቀት ዋዜማ ቀጥሎ፡ በታኅሣሥ ፴ ቀን ያበቃል። መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
በቅዱሱ ኪዳን ወንድማችንና የአገልግሎት ተባባሪያችን፡ ኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን፡ ‘ከዚህ ቀደም፡ አገራችን ኢትዮጵያ ላይ ደርሶ የነበረው ረኃብ፡ በሌሎች አገሮች ላይ ደርሶና አስከፊ ዕልቂት አስከትሎ ካለፈው ኹሉ፡ እንዲህ ጎልቶና ገንኖ በመላው ዓለም ዕውቅናን ሊያገኝ የቻለበት፡ ለእኛም ለኢትዮጵያ ሰዎች፡ ዋና መገለጫ የኾነበት ምክንያት ምንድን ነው?’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ጽሑፍ፡ የኅዋ-ሰሌዳችን ታዳሚዎች እንድትመለከቱት ይኸው ቀርቦላችኋል። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
በቅዱሱ ኪዳን ወንድማችንና የአገልግሎት ተባባሪያችን፡ ኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን፡ ‘ከዚህ ቀደም፡ አገራችን ኢትዮጵያ ላይ ደርሶ ስለነበረው ረኃብና እንዲህ ጎልቶና ገንኖ በመላው ዓለም ዕውቅናን ሊያገኝ የቻለበት፡ ለእኛም ለኢትዮጵያ ሰዎች፡ ዋና መገለጫ የኾነበት ምክንያት ምንድን ነው?’ በሚል ርዕስ ላዘጋጀው ጽሑፍ፡ ከኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት የተሰጠውን መንፈስ ቅዱሳዊ ምላሽ፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
በኹለንተናው፡ ሓሤት እና ምስጋና ብቻ የተመላው፣ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የቅዱስ ኪዳኗ ኢትዮጵያ ልጆች፡ ለዝንተ-ዓለም ሲገለገሉበትና ሲያገለግሉበት የኖሩት፣ ከበዓለ-ኢትዮጵያ የቅዳሴ ጸሎት በፊት የሚደረገውን፡ ሥርዓተ-ጸሎት፡ ትመለከቷቸው፥ ትገለገሉባቸውም ዘንድ፥ እንሆ! በኅዋ-ሰሌዳችን አሥፍረንላችኋል። በመቅረጸ-ድምፅ እየተዘጋጀ ያለው፡ የሥርዓተ-ጸሎቱ አቅርቦት፡ ፈቃደ-እግዚአብሔር ኾኖ እንደተጠናቀቅ፡ በተገቢው ሥፍራ እንደሚቀርብላችሁ ከወዲኹ ልናሳውቃችሁ እንወድዳለን። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ልዑል እግዚአብሔር፡ ከረዥም ዘመናት በኋላ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፥ በሰማይ እና በምድር ፍጥረታተ-ዓለማቱም ኹሉ፣ በኢትዮጵያዊው የእግዚአብሔር እውነት እና የመንፈስ-ቅዱስ ሥርዓተ-አምልኮ፣ ለ፯ሺ፭፻፱ ዓመታት፡ ከጥር ፳፰ እስከ፴ ቀን ለሚከበረው ለዘንድሮው የ፳፻፱ (፪ሺ፱) ዓመተ-ምሕረቱ በዓለ-ኢትዮጵያ፣ እንኳን፡ በደኅና እና በሰላም አደረሰን! በያለንበትም፡ ልንቀደስበት በቃን! መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ይድረስ፦ ለተወደዳችሁ፡ የክህነት ባልደረቦቼ፡ ኪዳናውያት እኅቶቼና ኪዳናውያን ወንድሞቼ! በእግዚአብሔራዊው ሰላማችን ኢየሱስ መሲሕ የጾሙ መታሰብያ ሓሤት ተመልተን፡ ኹላችንም፡ በእያለንበት፡ ከነቤተሰቦቻችን፡ በመልካሙ ሕይወታችን እንደምንገኝ፣ ለዚህ ቸርነቱም፡ ፈጣሪያችንን፡ ከነእናቱ፡ ያለማቋረጥ እንደምናመሰግን አምናለሁ። ይህን እ-ጦማር የጻፍሁላችሁ፡ በዚሁ፡ በጾሙ መታሰብያ ጊዜ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ አንድ እንግዳ ተአምር ደርሶ ስለታየ፡ የእርሱን፡ የምሥራች ዜና ላሰማችሁ ብዬ ነው፤ እርሱም፡ እነሆ፦ |
ፈጣሪያችንና አምላካችን ኢየሱስ መሲሕ፡ ምንጊዜም ከማትለየው፡ ከእግዝእተብሔር ቅድስት እናቱና እናታችን ድንግል ማርያም ጋር፡ አስቀድሞ፡ በዓለ-ኢትዮጵያን፥አከታትሎም፡ ተዝካረ-ኪዳነ ምሕረትንና ዓቢይ-ጾምን አስፈጽሞ፡ ለዘንድሮው በዓለ-ሆሣዕናና ዝክረ-ሰሙነ ሕማማት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅና አደረሰን! ይድረስ፡- በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎች፣ ካህናት ኾናችሁ “ኢትዮጵያ” በተባለችው አገር ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ ኪዳናውያት እኅቶችና ኪዳናውያን ወንድሞች! |
ይደረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፡"ኢትዮጵያ" በተባለችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት! በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ኢትዮጵያዊዉን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋለን። |
በመጋቢት እና በሚያዝያ ወሮች መግቢያ፥ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት፣ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፦ |
የመጀመሪያ ክፍል፤ እኛ፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ የአንድ እናት እና የአንድ አባት ልጆች መኾናችንን ለመግለጽ የምንጠቀምበት፡ ''ወንድሜ''፣ ወይም፡ ''ወንድምዬ''፣ ''እኅቴ''፣ ወይም፡ ''እኅትዬ'' የሚሉት የተዘምዶ ስሞች፡ ትክክለኛ ትርጓሜያቸውን እንደምናውቅ ይታመናል፤ ይኽውም፡ ''ወንድም'' የሚለው፡ የኢትዮጵያኛ ቃል፡ ''ወልደ-እም'' ከሚለው የግእዝ ሓረግ የተወረሰ ሲኾን፥ ፍቺው፡ የ''እናት-ልጅ'' ማለት ነው፤ ''እኅት'' የሚለው የግእዝ ቃል ደግሞ፡ ቀጥተኛ ትርጓሜው፡ ''በሴትነት አካልና ባሕርይዋ፡ የእናት አምሳያ የኾነች!'' ተብሎ ይፈታል። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...
|
ቃለ ዐዋድ! እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር። የአዋጅ ቃል! ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት። ለዚህ፡ የዐዋጅ ቃል፡ መነሻ የኾነው ምክንያት፡ ለእውነተኞች ልጆቻችን፡ ለመናገርም፣ ለመስማትም፡ ሊያሠቅቋችሁ የሚችሉ፣ ነገር ግን፡ ሓሰት በመኾናቸው፡ በእኛዪቱ እግዚአብሔራዊት እውነት፡ አማናዊነታቸው የተነገረላቸው ኹለት ቍም-ነገሮችን ስለያዘ፡ አርእስተ-ጉዳይ ነው፤ እርሱም፦ |
እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው! ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምስጋና ጾም-ጸሎታችን የምንፈጽማት፡ በአዲሱ መለኮታዊ የዐዋጅ ቃል መንፈስና ዘመን ይኾናል። ሙሉውን ምንባብ ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ! ... |
'የድንግል ማርያም መልእክተኛ ነኝ!' እና 'ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ነኝ!' እያሉ ስለሚቀርቡ ሰዎች፡ በኪዳናውያን መካከል የተደረገ መጻጻፍ በሚል ርእስ የተከወነ አጭር ዝግጅት። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ለእኛ፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ከዓበይት ይህ በዓል፡ ከመድኃኒታችን፡ ከእግዝእትነ [እግዝእተብሔራችን] እም፡ ድንግል ማርያም፡ በሰውነት የተወለደው፡ ሰላማችን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ፡ በዐጸደ ሥጋ፡ ዐብረውት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መካከል፡ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፥ ወንድሙንም ዮሓንስን፥ በዐጸደ ነፍስ ካሉት ባለሟሎቹ ደግሞ፡ ሙሴንና ኤልያስን፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በሚገኘው፡ "ታቦር" በተባለው፡ የወይራ ዛፍ ተራራ ላይ አምጥቶ፡ የባሕርይ አምላክነቱን በመግለጥ፡ ታማኞች አገልጋዮቹ፡ ሊያዩ የተመኙትን፡ እንዲያዩ፥ ሊሰሙ የተመኙትንም፡ እንዲሰሙ ያደረገበት ቸርነቱና ኃይሉ የሚዘከርበት ነው። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ቍጥር ፲፱/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ ዐዋድ! እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር። የአዋጅ ቃል! ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት። "መጽሓፍ ቅዱስ"ን በተመለከተ። በአኹኑ ጊዜ፡ "መጽሓፍ ቅዱስ" የሚባለው፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ፣ በተለይ፡ ብሉያቱ፡ እውነተኞቹ የእስራኤል ልጆች ሳይኾኑ፡ ራሳቸውን፡ "የእስራኤል ልጆች" የሚሉት፡ ኦሪታውያኑ አይሁድ የጻፉት ስለኾነ፡ የኢትዮጵያ ልጆች መጽሓፍ አይደለም። ይህም እውነታ፡ የገናናዎቹ እና የስመ-ጥሩዎቹ፡ የእነመልከ-ጼዴቅ እና የእነንግሥት ማክዳ፣ እነርሱን የመሰሉትም ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ዜና- መዋዕል እና ዝክረ-ነገር፡ ተሟልቶ እና ተስተካክሎ የተመዘገበበት ባለመኾኑ ጭምር፡ ተረጋግጦ ይታወቃል። |
የ፳፻፱ ዓ.ም. የፍልሰታ ማርያም በዓል መልእክት። ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል። "ፍልሰታሃ ለማርያም!" በሚል ስያሜ፡ ነሓሴ ፲፮ ቀን የምትከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ የፍልሰቷ መታሰቢያ በዓለ ዕለት ዝክረ ነገር፡ እንዲህ ነው፦ |
በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የተፈጸመው፡ የኪዳናዊ አክሊሉ መልአኩ ብርዝነሽ፡ ወስመ-ጥምቀቱ፡ አክሊለ-ሰማዕት እና የኪዳናዊት ቤዛዊት ስንሻው ንጋቷ፣ ወስመ-ጥምቀታ፡ ዕሴተ-ገብርኤል ሥርዓተ-ተክሊል፣ በዓለ-ከብካብ እና የሠርግ ድግስ። መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ልዑል እግዚአብሔር፡ |
ከመስከረም ፩፡ ርእሰ-ዐውደ-ዓመት፡ እስከኅዳር ፳፩ ቀን፡ ተዝካረ-ማርያም ድረስ ስላሉ በዓላትና አጽዋማት፡ መልእክታዊ ማብራሪያ። የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም በዓለ ልደት። [በግእዙ፡ "እግዝእትነ"፡ "እግዝእተብሔራችን" እንጂ፡ "እመቤታችን" ማለት አይደለም፤ ከመስከረም ፩ ቀን፡ የርእሰ ዐውደ-ዓመት በዓል ጋር፡ ዐብሮ ስለሚታሰበው፡ ስለእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ የልደቷ በዓል፡ እዚህ ላይ፡ ሊታወስ የሚገባው ቍም-ነገር አለ። ያንንም፡ እንደሚከተለው ገላልጠን አቅርበንላችኋል፦ ሙሉውን መልእክት ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
በያለንበት፡ በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፥ የምትጠብቀንንና የምትመራንን፡ ቸሪቱን ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያመሰገንን፥ "እንኳን ጾመ-ነቢያትን በሰላም አስፈጽሞ፡ ለበዓለ-ትስብእት ሥርዓተ-ሕይወታችን አደረሰን!" እያልን፥ በሰማዩ አባታችንና በሰማይዋ እናታችን ቅዱስ ስም፡ የተከበረ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን። የ፳፻፲ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መንፈስ ቅዱሳዊ መልእክት፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋልና በተለመደው የጥሞና መንፈስ ኾናችሁ ተከታተሉት። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ በኢትዮጵያዊው ሥርዓት፡ ጥር ፩ ቀን ለሚከበረው፡ ለ፳፻፲ (፪ሺ፲)ኛው ዓመት የሰላማችን የኢየሱስ መሲሕ ጥምቀት፣ እንዲሁም፡ ለተአምራዊው የቃና ዘገሊላ ሠርግ፥ ለመድኃኒታችን ድንግል-ማርያም ሰማያዊ ፍልሰትና ለኪዳነ ምሕረት በዓላት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅንነትና በሰላም አደረሰን! የእናቲቱ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም እና የልጇ የወዳጇ የእግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕ በዓላተ-ትስብእት፡ በእርሱ፡ በታኅሣሥ ፩ዱ ቀን ተጀምሮ፡ በእርሷው፡ በታኅሣሥ ፯ቱ ቀን በኩልም ዐልፎ፣ የረቡዕና የዓርብ ጾምም እንኳ ሳይኖርበት፡ በፍጹሙ የጾመ-ማርያምነት መንፈሳዊ ደረጃ እየተካኼደ፡ "ከተራ" እስከሚባለው፣ በአንዲት ቀን የጋድ ጾም እስከሚዘከረው፡ እስከጥምቀት ዋዜማ ቀጥሎ፡ በታኅሣሥ ፴ ቀን ያበቃል። መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
የ፳፻፲ቱ (የሃያ መቶ ዐሥሩ=የኹለት ሺ ዐሥሩ) ዓመተ-ምሕረት ዓቢይ ጾም። ይኸውም፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፥ የክፋትና የሓሰት፥ የጥፋትና የሞት አባት የኾነው ዲያብሎስ፡ ከነጭፍሮቹ፡ አሢሮ የቀፈቀፈውንና |
ቸሩ እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ለ፳፻፲ (፪ሺ፲)ኛው ዓመተ-ምሕረት፡ በዓለ-ትንሣኤ፡ በያለንበት አደረሰን! ይድረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፥ «ኢትዮጵያ» በተባላችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት! በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም፡ ኢትዮጵያዊውን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋላን። |
|
ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፲ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] አሥረኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን! እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው! ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምስጋና ጾም-ጸሎታችን የምንፈጽማት፡ በአዲሱ መለኮታዊ የዐዋጅ ቃል መንፈስና ዘመን ይኾናል። |
የ፳፻ ፲ ዓ.ም. የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል መልእክት። ለእኛ፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ከዓበይት በዓሎቻችን፡ አንዱ የኾነው፡ በዓለ ደብረ-ታቦር የሚውለው፡ በነሓሴ ፲፫ ቀን በመኾኑ፡ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ፡ ልዩ ምዕራፍ ኾኖ፡ በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦና ማኅሌት ይከበራል። ይህ በዓል፡ ከመድኃኒታችን፡ ከእግዝእትነ [እግዝእተብሔራችን] እም፡ ድንግል ማርያም፡ በሰውነት የተወለደው፡ ሰላማችን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ፡ በዐጸደ ሥጋ፡ ዐብረውት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መካከል፡ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፥ ወንድሙንም ዮሓንስን፥ በዐጸደ ነፍስ ካሉት ባለሟሎቹ ደግሞ፡ ሙሴንና ኤልያስን፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በሚገኘው፡ "ታቦር" በተባለው፡ የወይራ ዛፍ ተራራ ላይ አምጥቶ፡ የባሕርይ አምላክነቱን በመግለጥ፡ ታማኞች አገልጋዮቹ፡ ሊያዩ የተመኙትን፡ እንዲያዩ፥ ሊሰሙ የተመኙትንም፡ እንዲሰሙ ያደረገበት ቸርነቱና ኃይሉ የሚዘከርበት ነው። |
የ፳፻፲ ዓ.ም. የፍልሰታ ማርያም በዓል መልእክት። ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል። "ፍልሰታሃ ለማርያም!" በሚል ስያሜ፡ ነሓሴ ፲፮ ቀን የምትከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ የፍልሰቷ መታሰቢያ በዓለ ዕለት ዝክረ ነገር፡ እንዲህ ነው፦ |
እኛ፡ የቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፡ "ሱባዔ ፍልሰታ" ካበቃች በኋላ፡ ኹለት ሳምንቶችን፡ በሥጋዊውና በመንፈሳዊው የፋሲካ ደስታና የሓሤት ድግስ ቆይተን፡ "ሱባዔ ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "የጳጉሜ ሱባዔ" ብለን፡ ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከል፡ አንዲቱ ኾና የምታስተናግደን፡ ትንሿ ሰሞን ትቀበለናለች። እርሷም፡ በመስከረም ፩ ቀን ለሚውለው፡ ለታላቁ የዐውደ ዓመት በዓላችን፡ ሰሙነ ዋዜማ የኾነችው፡ የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን እና ሱባዔያችን ናት። መልእክቱን ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
ርእሰ አንቀጽ እግዚአብሔርን፥ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ልጆች በሚመለከት፡ በብሉዩ ኪዳን ነቢይ፦"እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ-ዓለም፤ ወገብረ መድኃኒተ፡ በማእከለ ምድር፤ አንተ አጽናዕካ፡ ለባሕር በኃይልከ፤ ወአንተ ሰበርከ ርእሰ-ከይሲ፡ በውስተ ማይ፤ ወአንተ ቀጥቀጥከ፡ አርእስቲሁ ለከይሲ። ወወሀብኮሙ ሲሳዮሙ፡ ለሕዝበ-ኢትዮጵያ! "ዓለሙን ከመፍጠርህ በፊትም ኾነ፡ በኋላ፡ ምንጊዜም፡ ንጉሣቸው የኾንከውና በምድር መካከል፡ መድኃኒትን [በኢትዮጵያዋ ድንግል ማርያም] ያደረግህ፥ ባሕርንም፡ በኃይልህ [በኢትዮጵያው ኢየሱስ መሲሕ] ያጸናህ፥ [በእርሱ፡ በሰላምህ]፡ የእባቡን ጭንቅላት፡ በውኃ ውስጥ የሰበርህ፥ የዘንዶውንም ራሶች የቀጠቀጥህ፡ አንተ እግዚአብሔር፡ የቅዱሱ ኪዳን ሕዝብህ፥ የቅድስት እናትህ፡ የድንግል ማርያምምልጆች ለኾኑት፡ ለኢትዮጵያ ሰዎች፡ የሚያስፈልጋቸውን ሲሳይ [ምግብን፣ ልብስን፣ መኖሪያን] ኹሉ ሰጠሃቸው!" ተብሎ የተነገረ የትንቢት ቃል መኖሩ ይታወቃል። |
ከመስከረም ፩፡ ርእሰ-ዐውደ-ዓመት፡ እስከኅዳር ፳፩ ቀን፡ ተዝካረ-ማርያም ድረስ ስላሉ በዓላትና አጽዋማት፡ መልእክታዊ ማብራሪያ። የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም በዓለ ልደት። [በግእዙ፡ "እግዝእትነ"፡ "እግዝእተብሔራችን" እንጂ፡ "እመቤታችን" ማለት አይደለም፤ ከመስከረም ፩ ቀን፡ የርእሰ ዐውደ-ዓመት በዓል ጋር፡ ዐብሮ ስለሚታሰበው፡ ስለእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ የልደቷ በዓል፡ እዚህ ላይ፡ ሊታወስ የሚገባው ቍም-ነገር አለ። ያንንም፡ እንደሚከተለው ገላልጠን አቅርበንላችኋል፦ ሙሉውን መልእክት ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
የ፳፻፲፩ዱ (የሃያ መቶ ዐሥራ አንዱ=የኹለት ሺ ዐሥራ አንዱ) ዓመተ-ምሕረት ዓቢይ ጾም። ይኸውም፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፥ የክፋትና የሓሰት፥ የጥፋትና የሞት አባት የኾነው ዲያብሎስ፡ ከነጭፍሮቹ፡ አሢሮ የቀፈቀፈውንና |
ፈጣሪያችንና አምላካችን ኢየሱስ መሲሕ፡ ምንጊዜም ከማትለየው፡ ከእግዝእተብሔር ቅድስት እናቱና እናታችን ድንግል ማርያም ጋር፡ አስቀድሞ፡ በዓለ-ኢትዮጵያን፥አከታትሎም፡ ተዝካረ-ኪዳነ ምሕረትንና ዓቢይ-ጾምን አስፈጽሞ፡ ለዘንድሮው በዓለ-ሆሣዕናና ዝክረ-ሰሙነ ሕማማት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅና አደረሰን! |
ይደረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፡ "ኢትዮጵያ" በተባለችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት! በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ኢትዮጵያዊዉን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋለን። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፪ሺ፲፩ (፳፻፲፩)ኛው ዓመተ ምሕረት፡ ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን! እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው! |
ከመስከረም ፩፡ ርእሰ-ዐውደ-ዓመት፡ እስከኅዳር ፳፩ ቀን፡ ተዝካረ-ማርያም ድረስ ስላሉ በዓላትና አጽዋማት፡ መልእክታዊ ማብራሪያ። [በግእዙ፡ "እግዝእትነ"፡ "እግዚአብሔርታችን" እንጂ፡ "እመቤታችን" ማለት አይደለም፤ ከመስከረም ፩ ቀን፡ የርእሰ ዐውደ-ዓመት በዓል ጋር፡ ዐብሮ ስለሚታሰበው፡ ስለእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ የልደቷ በዓል፡ እዚህ ላይ፡ ሊታወስ የሚገባው ቍም-ነገር አለ። ያንንም፡ እንደሚከተለው ገላልጠን አቅርበንላችኋል፦ መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!... |
የ፪ሺ፲፪ (፳፻፲፪) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት። ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ሉቃስ፡ ወደዘመነ ዮሓንስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡ |
በያለንበት፡ በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፥ የምትጠብቀንንና የምትመራንን፡ ቸሪቱን ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያመሰገንን፥ "እንኳን ለጾመ-ነቢያት ሥርዓተ-ሕይወታችን ቅበላ አደረሰንም!" እያልን፥ በሰማዩ አባታችንና በሰማይዋ እናታችን ቅዱስ ስም፡ የተከበረ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን። የ፳፻፲፪ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መንፈስ ቅዱሳዊ መልእክት፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋልና በተለመደው የጥሞና መንፈስ ኹናችሁ ተከተታተሉት። |
ይደረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፡ "ኢትዮጵያ" በተባለችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት! በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ኢትዮጵያዊዉን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋለን። |
ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፪ሺ፲፪ (፳፻፲፪)ኛው ዓመተ ምሕረት፡ ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን! እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው! ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምስጋና ጾም-ጸሎታችን የምንፈጽማት፡ በአዲሱ መለኮታዊ የዐዋጅ ቃል መንፈስና ዘመን ይኾናል። |
ፍልሰታሃ ለማርያም! ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል። አግሃደት ፍልሰታሃ፡ ማርያም ድንግል! በከመ ትንሣኤ ወልዳ፡ ዘልዑል! ድንግል ማርያም፡ ፍልሰቷን ገለጠች! የልጇን ትንሣኤ፡ በእርሱ አስመሰለች! ልዑል እግዚአብሔር፡ሃይማኖታችንና አገራችን፥ እናታችንና ንግሥታችን፡መድኃኒታችን እግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡ ከምድር ወደሰማያት የተመለሰችበትን፡ የፍልሰቷን በዓል፡ ዘንድሮም፡ በ፳፻፲፪ተኛው (ኹለት ሽህ፡ ዐሥራኹለተኛው) ዓመተ-ምሕረት፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ እንኳን፡ በሰላም ለማክበር አበቃን! መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!.. |
ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ዮሓንስ፡ ወደዘመነ ማቴዎስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡ መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!... |
በያለንበት፡ በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፥ የምትጠብቀንንና የምትመራንን፡ ቸሪቱን ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያመሰገንን፥ "እንኳን ለጾመ-ነቢያት ሥርዓተ-ሕይወታችን ቅበላ አደረሰንም!" እያልን፥ በሰማዩ አባታችንና በሰማይዋ እናታችን ቅዱስ ስም፡ የተከበረ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን። የ፳፻፲፫ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መንፈስ ቅዱሳዊ መልእክት፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋልና በተለመደው የጥሞና መንፈስ ኹናችሁ ተከተታተሉት።
|