ከዮሓንስ ኢትዮጲስ ለቀረቡ ጥያቄዎች፡ ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወ.ኢ. የተሰጡ መልሶች፥ ከእንግሊዝኛው ወደኢትዮጵያኛ፡ በኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን የተተረጎመው ተከውኖ።

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡

ተደብቀው የኖሩ፡ አዳዲስ ምሥጢራትን የገለጠችባቸው፣

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ ለቀረቡ፡
ተከታታይ ጥያቄዎች፡ የተሰጡ መልሶች።
 
ኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን፡
ከእንግሊዝኛው ዝግጅት፡ ወደኢትዮጵያኛው እንደተረጐመው፤

አብርሆትና አርትዖት፡ በኪዳናዊ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ (ንቡረ-እድ)

+   +   +

ከዮሓንስ ኢትዮጲስ፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ፡ ፩ደኛ ጥያቄ፡-

     ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾኑ፡ ማረጋገጫዎ ምን እንደኾነ ልጠይቅዎ ግድ ይለኛል? የትኛው መጽሓፍ ቅዱስ፡ ይህን ይናገራል? ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ከኾነ፣ "የጥንቶቹ አይሁድ፡ ከኢትዮጵያውያን ጋር፡ በአካል ተመሳሳይ ነበሩ፤" ማለት ነው?

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የሰጠችው መልስ፡-

     በጥያቄዎ ላይ፡ ሌላ ጥያቄ እንጨምራለን። ጥያቄያችን፡ ቀላልና ግልጽ ሲኾን፡ እርስዎ ከጠየቁን ጋር፡ ተመሳሳይ ነው። ልዩነቱ፡ ጥያቄያችን ያነጣጠረው፡ እርስዎው እራስዎ ላይ መኾኑ ነው። ለጥያቄያችንም፡ እውነተኛውን ምላሽ እንዲሰጡን፡ በትሕትና እንጠይቅዎታለን።
     ጥያቄያችንም፡ "እርስዎ ራስዎ፡ ኢትዮጵያዊ ስለመኾንዎ፡ ማለትም፡ ስለእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ማንነትዎ፡ ማረጋገጫዎ ምንድን ነው?" የሚል ነውና፡ እባክዎ! ለዚህ ጥያቄያችን፡ የተሟላ መልስዎን ይስጡን?
     ይኽን የጠየቅንዎ፡ በጥያቄዎ ላይ ላነሡት ርእስ፡ በመጻሕፍታችንና በኅዋ ሰሌዳችን፥ እንዲኹም፡ በፌስቡካችን ላይ፡ በዝርዝር የቀረበ ሰፊ ማብራሪያ ስለሚገኝ፡ ትክክለኛውን ግንዛቤ ለማግኘት እንደሚረዳዎ፡ ለመጠቆም በማሰብ ነው።