የቆሼ መልእክት፣ ከአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ ከግብፁ ዕልቂት ጋር።

በመጋቢት እና በሚያዝያ ወሮች መግቢያ፥ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት፣
በኢትዮጵያ ምድር እና በግብፅ አገር የደረሱት ዕልቂቶች
መለኮታዊ መልእክት፡
ምንድር ነው?

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፦
፩ኛ፡ በኢትዮጵያዋ አዲስ አበባ መናገሻ ከተማ ክልል በምትገኘው፡ "ቆሼ" በምትባለው መንደር፡ በመጋቢት ፪ ቀን፥ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት፣ 
፪ኛ፡ በግብፅ ምድር፡ በካይሮና በእስክንድርያ ከተማዎች፡ ሚያዝያ ፩ ቀን፣ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት የደረሱትን ጥቃት እና ዕልቂት በሚመለከት፡ በኪዳነ-ምሕረቱ ጸጋና በረከት፡ ሙታኑ፡ ዕረፍተ-ነፍስን፥ ቋሚ ቤተሰቦቻቸውም፡ መጽናኛውን መንፈስ እንደሚያገኙ በማመንና በመተማመን፣ ከዚህ የሚከተለውን መለኮታዊ መልእክት፡ ለቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆቿ ታስተላልፍ ዘንድ፡ አግባብ ኾኖ አግኝታዋለች።

፩ኛ. በዓለም ላይ ሠፍረው በሚገኙት የሕዝቦቿና የአሕዛቧ ኅብረተ-ሰብ መካከል፡ በድንገተኛ አደጋ ረገድ፡ እስከዛሬ ሲሰማ የተኖረው የዕልቂት መርዶ፡ የመሬት መደርመስ፣ ወይም፡ የሕንፃ መደርባት፣ ከዚያም ቢያልፍ፡ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታንና የሰደድ እሳትን፣ የዝናብ ውሽንፍርንና የውኃ ጎርፍን፥ ወይም፡ የዐውሎ-ነፋስንና የማዕበል ማጥለቅለቅን፥ ደግሞም፡ የመሬት ነውጥንና የበረዶ ፍልሰትን በመሰሉ፣ በተፈጥሮ ኃይላት ምክንያት የሚደርሱ፤ ድንገተኛ አደጋዎች ያስከተሉ የጥፋት ዓይነቶች ብቻ ነበር።

ዛሬ ግን፡ ሰዎች፡ "ራሳቸው የከመሩት ቍሻሻ ተደርምሶ፥ ወይም ተደርብቶ፡ በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ፡ የሞትና የአካል ጉዳትን አስከተለ!" የሚል አሳዛኝና አሳፋሪ ወሬ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰማ።

መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...