አዲስ አበባ፣ ቆሼ

የቆሼ መልእክት፣ ከአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ ከግብፁ ዕልቂት ጋር።

በመጋቢት እና በሚያዝያ ወሮች መግቢያ፥ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት፣
በኢትዮጵያ ምድር እና በግብፅ አገር የደረሱት ዕልቂቶች
መለኮታዊ መልእክት፡
ምንድር ነው?

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፦
፩ኛ፡ በኢትዮጵያዋ አዲስ አበባ መናገሻ ከተማ ክልል በምትገኘው፡ "ቆሼ" በምትባለው መንደር፡ በመጋቢት ፪ ቀን፥ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት፣ 
፪ኛ፡ በግብፅ ምድር፡ በካይሮና በእስክንድርያ ከተማዎች፡ ሚያዝያ ፩ ቀን፣ ፳፻፱ ዓመተ-ምሕረት የደረሱትን ጥቃት እና ዕልቂት በሚመለከት፡ በኪዳነ-ምሕረቱ ጸጋና በረከት፡ ሙታኑ፡ ዕረፍተ-ነፍስን፥ ቋሚ ቤተሰቦቻቸውም፡ መጽናኛውን መንፈስ እንደሚያገኙ በማመንና በመተማመን፣ ከዚህ የሚከተለውን መለኮታዊ መልእክት፡ ለቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆቿ ታስተላልፍ ዘንድ፡ አግባብ ኾኖ አግኝታዋለች።