''እኔ፡ ማን ነኝ? ምንድር ነኝ?'' በሚል ርእስ፡ በሦስት ክፍል ተዘጋጅቶ የቀረበ መጠነኛ ማብራሪያ፤ በኪዳናዊ ኃይለ-ማርያም።

የመጀመሪያ ክፍል፤

እኛ፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ የአንድ እናት እና የአንድ አባት ልጆች መኾናችንን ለመግለጽ የምንጠቀምበት፡ ''ወንድሜ''፣ ወይም፡ ''ወንድምዬ''፣ ''እኅቴ''፣ ወይም፡ ''እኅትዬ'' የሚሉት የተዘምዶ ስሞች፡ ትክክለኛ ትርጓሜያቸውን እንደምናውቅ ይታመናል፤ ይኽውም፡ ''ወንድም'' የሚለው፡ የኢትዮጵያኛ ቃል፡ ''ወልደ-እም'' ከሚለው የግእዝ ሓረግ የተወረሰ ሲኾን፥ ፍቺው፡ የ''እናት-ልጅ'' ማለት ነው፤ ''እኅት'' የሚለው የግእዝ ቃል ደግሞ፡ ቀጥተኛ ትርጓሜው፡ ''በሴትነት አካልና ባሕርይዋ፡ የእናት አምሳያ የኾነች!'' ተብሎ ይፈታል።

መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...