የዓውደ ዓመቱ፡ ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡
ከዘመነ ማርቆስ ወደዘመነ ሉቃስ አሸጋግሮ፡

የ፯ሺ፭፻፯ (የሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባተ)ኛውን ዓመት፡
የነጻነት ህልውናችንን በዓል፥

የ፪ሺ፯ (የኹለት ሺህ ሰባተ)ኛውን ዓመት፡
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን፤
የ፪ሺ፳፫ (የኹለት ሺህ ሃያ ሦሥተ)ኛውን ዓመት፡
የእመቤታችን ድንግል ማርያምን
የልደታት በዓል ለማክበር ለበቃንበት፡

ለአዲሱ የ፪ሺ፯ (፳፻፯)
(ኹለት ሺህ ሰባት፤ ወይም፡ ሃያ መቶ ሰባት፤ ወይም፡ ዕሥራ ምዕት ወሰብዓቱ)
ዓመተ ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፤

ደግሞም፡
ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በዓላተ ግዝረት፤ በዓተ መቅደስና ስደት፥
እንዲሁም፡ ለዕፀ መስቀሉ የደመራና የበዓሉ ዕለት፥
ለእመቤታችንም፡ በዓለ ዕርገት፡

እንኳን በያለንበት በሰላም አደረሰን!

+++