ጾመ ጳጉሜ
"ጾመ ጳጉሜ"
እኛ፡ የቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፡ "ጾመ ፍልሰታ" ካበቃች በኋላ፡ ኹለት ሳምንቶችን፡ በሥጋዊውና በመንፈሳዊው የፋሲካ ደስታና የሓሤት ድግሥ ቆይተን፡ "ጾመ ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "የጳጉሜ ጾም" ብለን፡ ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከል፡ አንዲቱ ኾና የምታስተናግደን፡ ትንሿ ሰሞን ትቀበለናለች። እርሷም፡ በመስከረም ፩ ቀን ለሚውለው፡ ለታላቁ የዐውደ ዓመት በዓላችን፡ ሰሙነ ዋዜማ የኾነችው፡ የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን ናት።
"ጳጉሜ" ምን ማለት ነው?
የ፯ሺ፭፻፯ ዓመታት ዕድሜን በሚያስቆጥረው፡ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ ሃይማኖታችን የቀን አቆጣጠር ሥርዓት፡ በግእዝ፡ "ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "ጳግሜ"፥ በሕዝባዊ አነጋገር ደግሞ፡ "ቋግሜ" የምትባለው፡ ግልገል ወር፦
፩ኛ፤ በዐውደ ዓመቱ መጨረሻ የሚገኝ፡ የ፭ (አምስት) ቀኖች ተሩብ "ተውሣክ"፥ ወይም፡ "ጭማሪ" ማለት ነው።
፪ኛ፡ ከዐውደ ወርኅ ስለተረፈና በዓመት መጨረሻ ስለተገኘ፡ "ተረፍ"፥ ወይም፡ "ትርፍ" ይባላል።
በዚህ ቀመር [አቆጣጠር] መሠረት፡ እያንዳንዳቸው፡ እኩል ፴ (ሠላሳ) ቀኖች ያሏቸው፡ ፲፪ (ዐሥራ ኹለት) ወራት፡ የዓመቱን ፫፻፷ (ሦስት መቶ ስድሳ) ቀኖች ብቻ ሲያስገኙ፡ የዓመቱን ዑደት [ዙረት] ፍጹም ምሉእ ለማድረግ፡ በጠቅላላ፡ ፭ (አምስት) ቀኖች፡ ከ፮ (ስድስት) ሰዓቶች ይተርፋሉ። በየ፬ (አራት) ዓመቱ ደግሞ፡ እነዚህ፡ የየዓመቱ ፮ ሰዓታት ሲደመሩ፡ ፳፬ (ሃያ አራት) ሰዓታት ይኾኑና፡ ፩ ቀንን ያስገኛሉ።
ስለዚህ፡ በ፫ቱ (ሦስቱ) ዓመታት፡ ማለትም፡ በዘመናተ ዮሓንስ፥ ማቴዎስና ማርቆስ፡ ፫፻፷፭ቱ ቀኖች እና እንደቅደም ተከተላቸው፡ የዘመነ ዮሓንሱ ፮ (ስድስት) ሰዓቶች፥ የዘመነ ማቴዎሱ ፲፪ (ዐሥራ ኹለት) ሰዓቶች እና የዘመነ ማርቆሱ ፲፰ (ዐሥራ ስምንት) ሰዓቶች እየኾነና እየተደመረ የቀጠለው፡ የየዓመቱ ቀመር፡ በ፬ኛው (አራተኛው) ዓመት፡ በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ ላይ፡ ፳፬ (ሃያ አራት) ሰዓቶች ኾኖ በመሙላት፡ ለ፩ (አንድ) ቀንነት ይበቃና፡ ዓመቱን፡ ፫፻፷፮ (ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት) ቀኖች ያደርገዋል።፩
መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...