ጾመ ፍልሰታ

ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፰ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ስምንተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፰ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ስምንተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

+ + +

መግቢያ

     እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው!

ጾመ ጳጉሜ

"ጾመ ጳጉሜ"

     እኛ፡ የቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፡ "ጾመ ፍልሰታ" ካበቃች በኋላ፡ ኹለት ሳምንቶችን፡ በሥጋዊውና በመንፈሳዊው የፋሲካ ደስታና የሓሤት ድግሥ ቆይተን፡ "ጾመ ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "የጳጉሜ ጾም" ብለን፡ ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከል፡ አንዲቱ ኾና የምታስተናግደን፡ ትንሿ ሰሞን ትቀበለናለች። እርሷም፡ በመስከረም ፩ ቀን ለሚውለው፡ ለታላቁ የዐውደ ዓመት በዓላችን፡ ሰሙነ ዋዜማ የኾነችው፡ የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን ናት።

"ጳጉሜ" ምን ማለት ነው?