ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፰ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ስምንተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!
Submitted by etkog12 on Fri, 08/05/2016 - 16:56ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፰ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ስምንተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!
+ + +
መግቢያ
እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው!