ለኪዳናውያትና ኪዳናውያን ባልደረቦቼ ማሳሰቢያ።

ተፈጸመ ትስብእት፡ በኢትዮጵያ ማርያም ድንግል!
በብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል፡ ዜናዌ ቃል!

ይድረስ፡ ለኪዳናውያት እና ለኪዳናውያን፡ "የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ልጆች"፥ እኅቶቼና ወንድሞቼ፥ የክህነት ባልደረቦቼም!

    በሰማያቱ የዘለዓለም አባታችንና እናታችን ስም፡ ከነቤተሰባችሁ፡ በያላችሁበት፡ "እንዴት አላችሁ!" እያልሁ፡ ኪዳናዊና ኢትዮጵያዊ ሰላምታዬን፡ አቀርብላችኋለሁ። ለእነርሱ፡ ምስጋናችን ይድረሳቸውና፡ ዐብረውኝ ካሉት ጋር፡ እኔ ደኅና ነኝ።
    ይህን ደብዳቤ እንድጽፍላችሁ መነሻ የኾነኝ ምክንያት፡ እንደተለመደው፡ ወደፊት፡ በመካከላችን፡ የደብዳቤ ልውውጥ በምናደርግበት ጊዜ፡ በዚህ ረገድ ያለውን የጽሕፈት አያያዛችንን አካኼድና የአሠራራችንን አፈጻጸም ለማቅለልና ለማቀላጠፍ ይቻለን ዘንድ፡ ልንከተለው ስለሚገባን ሥርዓት፡ አሳብ ላቀርብላችሁ ስለፈለግሁ ነው።