የ፳፻፰ ዓ.ም. ሚያዝያ ወር ቀን መቍጠሪያ ሠንጠረዥ ማስተካከያ

ዮም ፍሥሓ ኮነ! 
በእንተ መዋዕለ ዓቢይ ጾም፡ ዘኢየሱስ መሲሕ! 

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

ይድረስ፦ ለተከበራችሁትና ለተወደዳችሁት አንባቢዎቻችን!

     በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን፡ በነፍስ፥ በሥጋና በመንፈስ፡ ልጆቹና ነጋሢዎቹ፥ ዜጎቹና አገልጋዮቹ ባደረገን፥ በዘለዓለሙ ህልውናችንም፡ ሕያው አባታችንና እናታችን፥ ወንድማችንና እኅታችን፥ ጓደኛችንና ሕይወታችን በኾነው፡ በቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ስም፡ ኪዳናዊዉን ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን፡ በያላችሁበት እናቀርብላችኋለን።

     ለዚህ መልእክታችን መነሻ የኾነን ምክንያት፡ በዘንድሮው የ፳፻፰ ዓመተ ምሕረት ቀን መቍጠሪያችን፡ የሚያዝያ ወር ሠንጠረዥ ላይ፡ በሚያዝያ ፪ቷ ዘለዓለማዊት ዕለተ እሑድ ሰንበት የሚውለው፡ የ"ገብር ኄር" በዓለ-ተዘክሮ መኾን ሲገባው፡ በስሕተት፡ "ኒቆዲሞስ" ተብሎ፡ ኋለኛው፡ ወደፊተኛው ተዛውሮ ስለተገኘ፡ ያን፡ ማስተካከል አስፈላጊ መኾኑ ነው።

     ስለዚህ፡ ለዚህ ለደረሰው ስሕተት፡ ይቅርታችሁን እየጠየቅን፡ ከዚህ የሚከተለውን ማስተካከያ መግለጫ፡ በአክብሮት አቅርበንችኋለን፤ ይኸውም፡ "በሚያዝያ ፪ቷ ዘለዓለማዊት ዕለተ እሑድ ሰንበት የሚውለው፡ በዓለ-ተዘክሮ፡ ቀዳሚው "ገብር ኄር" ኾኖ፡ በተከታይዋ፡ በሚያዝያ ፱ኟ ዘላለማዊት እሑድ ሰንበት የሚውለው ደግሞ፡ የ"ኒቆዲሞስ" በዓለ ተዘክሮ መኾኑን እንድታውቁት ይኹን!" የሚለው ነው።

መልእክቱን፡ በነባራዊው የሰነድ ቅጽነት ለመመልከት፡ ከታች የተመለከተውን መጠቈሚያ ይጫኑ!...