የቀን መቍጠሪያ ሠንጠረዥ፥ መጋቢት ፲፩ ቀን፥ ፳፻፰ ዓ.ም. (20 March 2016)

የ፳፻፰ ዓ.ም. ሚያዝያ ወር ቀን መቍጠሪያ ሠንጠረዥ ማስተካከያ

ዮም ፍሥሓ ኮነ! 
በእንተ መዋዕለ ዓቢይ ጾም፡ ዘኢየሱስ መሲሕ! 

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

ይድረስ፦ ለተከበራችሁትና ለተወደዳችሁት አንባቢዎቻችን!

     በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን፡ በነፍስ፥ በሥጋና በመንፈስ፡ ልጆቹና ነጋሢዎቹ፥ ዜጎቹና አገልጋዮቹ ባደረገን፥ በዘለዓለሙ ህልውናችንም፡ ሕያው አባታችንና እናታችን፥ ወንድማችንና እኅታችን፥ ጓደኛችንና ሕይወታችን በኾነው፡ በቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ስም፡ ኪዳናዊዉን ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን፡ በያላችሁበት እናቀርብላችኋለን።