የ፳፻፯ ዓ.ም. የበዓለ ትስብእት፡ ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡
የዛሬ ኹለት ሺህ ሰባት ዓመት፡
በታህሣሥ አንድ ቀን፡
ባለሟሉን መልአክ፡ ቅዱስ ገብርኤልን፡
ወደቅድስቲቱ ኢትዮጵያዊት ድንግል ማርያም ልኮ፡
“ወናሁ ትፀንሲ! ወትውልዲ ወልደ!
ወትሰምይዮ ስሞ ኢየሱስ!”
ማለትም፡
“እንሆ ትፀንሻለሽ! ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ!
ስሙንም፡ ‘ኢየሱስ’ ትይዋለሽ!”
ሲል በተናገረው አምላካዊ ቃሉ፡
“ታላቁን፡ መለኮታዊና ዘለዓለማዊ ምሥራች!”
ለፍጥረት ዓለሙ ላሰማባት፡
ለዚች፡ ለ፪ሺ፯ (፳፻፯)ተኛው
የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትስብእት፡
(የፅንሰቱና የብሥራተ ገብርኤል)
እና
ታህሣሥ ፯ ቀን ለሚውለው፡
ለቅድስት ድንግል ማርያም የፅንሰቷ በዓል፡
በያለንበት፡ እንኳን በደኅና አደረሰን!