በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የተዘጋጀ፡ የታላቁ፡ የ፳፻፲ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መልእክት።

በያለንበት፡ በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፥ የምትጠብቀንንና የምትመራንን፡ ቸሪቱን ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያመሰገንን፥ "እንኳን ጾመ-ነቢያትን በሰላም አስፈጽሞ፡ ለበዓለ-ትስብእት ሥርዓተ-ሕይወታችን አደረሰን!" እያልን፥ በሰማዩ አባታችንና በሰማይዋ እናታችን ቅዱስ ስም፡ የተከበረ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን።

የ፳፻፲ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መንፈስ ቅዱሳዊ መልእክት፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋልና በተለመደው የጥሞና መንፈስ ኾናችሁ ተከታተሉት።