የ፪ሺ፲፪ (፳፻፲፪) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

የ፪ሺ፲፪ (፳፻፲፪) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ሉቃስ፡ ወደዘመነ ዮሓንስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡
የ፯ሺ፭፻፲፪ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዐሥራ ኹለተ)ኛውን ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል፣
እንዲሁም፡
የአዳምና የሔዋንን ልደት፥ የቅዱሱ ኪዳን፡ መነሻ የኾነው ሥርዓተ ጋብቻም የተከሠተበትን ቀን ያካተተውን፡ የፍጥረትን መገኛ ፯ሺ፭፻፲፪ኛውን ዓመት በዓል፥
ደግሞም፡ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያምን፡ የ፪ሺ፳፰ (የኹለት ሽህ ስምንተ)ኛውን ዓመት
እና
የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን፡ የ፪ሺ፲፪ (የኹለት ሽህ ዐሠራኹለተ)ኛውን ዓመት፡ የልደታት በዓል
ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ፡ የ፪ሺ፲፪ (፳፻፲፪)(ኹለት ሽህ ዐሥራኹለት፥ ወይም፡ ሃያ መቶ ዐሥራኹለት፥ ወይም፡ ዕሥራ ምእት ወዐሠርተክልኤቱ) ዓመተ-ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣ እንኳን፡ በያለንበት፡ በሰላም አደረሰን!

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...