ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!

ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት አገልግሎት፡ ከመላው ዓለም፡ ቁም-ነገር ያዘሉ በርካታ ጥያቄዎች ተቀብላ ማስተናገድ ከጀመረች፡ እነኾ በርካታ ዓመታት አስቆጥራለች። ለዕድምተኞቻችን፥ ለተከታታዮቻችን፥ ለአገርና ወገን፡ እንዲኹም፡ ለወደፊት ቋሚ ቅርስ እንደሚኾን በማመን፡ የምታስተናግዳቸው እነዚኽ ጥያቄዎች፡ ተገቢ መኾናቸው ቢታመንም፡ አንዳንዶቹ ጥያቄዎች፡ ምናልባት፡ ኹሉም፥ አለዚያ፡ አብዛኛዎቹ፡ ቀደም ብለው ቀርበውልን መልስ በሰጠንባቸው፦

፩ኛ፡ ንቡረ-እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ ባዘጋጇቸውና ዝርዝራቸው፡ በኅዋ-ሰሌዳችን ላይ በሠፈሩት መጻሕፍቶቻችን ውስጥ ተጠቃልለው ሊገኙ ስለሚችሉ፥

፪ኛ፡ በኅዋ ሰሌዳችንና በፌስቡክ መድረካችን ላይ ያሉትን "የጥያቄ እና መልስ" አብያተ-መዛግብታችንን በመክፈት፡ በእነዚህ መዛግብት ውስጥ ሳይካተቱ እንደማይቀሩ ስለምናምን፡

፫ኛ. በዚኸ፡ ‘ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!’ በሚል ርእስ፡ በተዘጋጀውና አብዛኛውን የተለመዱ ጥያቄዎች ሊያካትት እንደሚችል ስለምናምን፡

በቅድሚያ፡ እነዚህን የዕውቀት መካናት፡ መርምራችኹ ካያችኹና ካጣራችኽ በኋላ፡ ለጥያቄዎቻችኹ መልስ የሚኾኑትን ጽሑፎች፡ በእነዚህ ሥፍራዎች ውስጥ አለመኖራቸውን ስታረጋግጡ፡ በዚያን ጊዜ፡ እነዚያን ያዘጋጃችኹትን ጥያቄዎች፡ ልታቀርቡልን ይቻላችኋል።

በዚህ የአሠራር ሥርዓታችን፡ የእናንተ ብቻ ሳይኾን፥ በይበልጥ ግን፡ የእኛም ጊዜና ጕልበት፡ ከመባከን መዳኑ በግልጽ ይታያልና፡ ይኸው የአሠራር ሥርዓታችን፡ በኹላችንም ዘንድ አጥጋቢና አስደሳች ውጤትን ሊያስገኝልን እንደሚችል በማመን፡ በዚሁ መልክና ይዘት እንዲፈጸም በማድረግ እንድትተባበሩን፡ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ወደተደጋጋሚ ጥያቄዎች ለመመለስ ይኽን ይጫኑት