ከአባ ወልደ-አረጋዊ (አባ ዳንኤል ተጫኔ)፡ በፌስ ቡክ አድራሻችን በኩል፡ የተላከ መልእክት።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ይድረስ እጅግ ለማከብርዎት ለምናፈክዎትም አባት
ንቡረ እድ ኤርምያስ

አባቴ አሁን ይህችን አጭር መልእክት የጻፍኩልዎት በጉም እየሱስ ገዳም እዳከናውን የተሰጠኝን ስራ አከናውኔ አ/አ እደተመለስሁ ነው አባቴ አቋምዎት አልገባኝም የትነው ያሉ ለምንስ ወዳገርዎ ባስቸኮአይ አይገቡም ምላሽዎን ላኩልኝ እዲህ ያልኩበት ከፍቅር ከናፍቆት ነው ብዙ የማይገቡኝን ምስጢራት በማየቴ እርስዎ በመንፈስ ቅዱስ ያልዎትን ቦታ ማወቄ ስውራን አብዝተው ሲሳሱሉዎ ማየቴ አሁን ደግሞ እርስዎ ለዘመናት የደከሙለት እውነት አፍርቶ የኢትዮጵያ ስውራን ሁሉ በታላቅ ግስጋሴ ላይ መሆናቸውን ባይኔ አይቸ ዳስሸ ሰአታት እደቀሩን አውቄ እለት እለት ልናገረው ያልተፈቀዱ ምስጢራትን አውቄ ነው እባክዎ አባቴ ደካማነቴን አይናቁት እሺ በሉኝ ወዳገርዎ ግቡ ቅዱሳንም አያስቸግሩ ማለቴ ለእውነት የደከሙትን እያሰቡ ስለርስዎ የሚያደርጉትን ያየው አይኔ ያውቃል እኔም አብዝቸ ናፈኩዎ በተረፈ በዚህ የማልገልጣቸው ብዙ ምስጢራት አሉ በሚወዱአት ድግል በስቸኩዋይ ወዳገርዎ ኑልን በተረፈ የሰጡኝን መጸሀፍ ሁሉ በነጻ እደሰጡኝ ብዙ ሰው እዲዲንበት በቤተ ክርስቲያን ቤተ መጸሀፍት በክበር ተቀምጦ ብዙዎች እየዳኑበት ነው በነጻ ሰው እዲዲንበት እደሰጡኝ እኔም ሳልሳሳ በነጻ ብዙዎት እዲያገኙት ሰጥቻለሁ በእውነትም ብዙዎች እየዳኑበት ነው ማረጋገጥ ከፈለጉ ሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ሰንበት ተ/ቤት ቤተ መጸሀፍት ተረክቦት ብዙዎች እደዳኑበት ምስክርነት ያገኛሉ እኔም አደራየን በመዋጣቴ ደስ ብሎኛል የሰጡኝን ወርቅ አልቀበርኩም
ልጅዎ አባ ወልደ አረጋዊ(ዳንኤል ተጫነ)

በስመ እግዚአብሔር አብ፥ ወወልድ፥ ወመንፈስ ቅዱስ፤
በስማ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል፣ ወላዲተ አምላክ፤
በኃይለ መስቀሉ፡ ለእግዚእነ፥ ወአምላክነ፥ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
 
ተፈጸመ ትስብእት፡ በማርያም ድንግል!
በብሥራተ ገብርኤል፡ ዜናዌ ቃል!

 
ይድረስ ለተወደዱና ለተከበሩ አባ ወልደ አረጋዊ!
       ደኅንነትዎን ያሳወቀኝ እ-ጦማርዎ ደረሰኝ፤ አስበው ስለጻፉልኝና በውስጡም ስላሠፈሯቸው መልካካም ቃላት፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!
       የሚያካኺዱት የመንፈስ ቅዱስ ተልእኮዎ ስለተሳካልዎ፡ ኹላችንንም ደስ ያሰኛል፤ ለኹሉ ዋጋውን የማያስቀሩ፡ የሚያገለግሏቸው ቸሩ እግዚአብሔር፥ እናት አገራችንና መንግሥቱ የኾነችው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም፡ የአገልግሎትዎን ዋጋ እንደሚከፍሉዎ እሙን ነው።
ስላቀረቡልኝ ጥያቄና ስለሳሰቡኝ ቍም ነገር፡ የምሰጥዎ መልስ ቢኖር፡ እንደሚከተለው ነው፦
       ማናቸውም፡ የሚደርሰውና የሚኾነው፥ የሚፈጸመውም ኹሉ፡ መልካሙን ኹሉ በወጠኑ፥ እያካኼዱ ባሉትና በሚያከናውኑት፡ በእነርሱ፡ በቅድስቲቱ እናትና በተወደጁ ልጇ በተዘጋጀው መለኮታዊ ዕቅድ መሠረት ብቻ ስለኾነ፥ ለፍጥረተ ዓለሙም ኹሉ፡ የሚሻለውና የሚበጀው፡ ያ ነውና፡ እኔም፡ አኹን፡ "ለኹሉም፡ የእነርሱ ፈቃድ ይኹን!" እላለሁ።
የእግዚአብሔር መንግሥት የኾነችው፡ የእናታችን ኢትዮጵያ አገልጋዮች የኾንነው፡ እኔም ኾንሁ፥ እርስዎ፥ ሌሎቻችንም ኹሉ፡ እነርሱ፡ ለአገልግሎት ሲጠሩን፡ "አቤት! እመት!"፥ ሲልኩንም፡ "ወዴት!" ብለን፡ ፈቃዳቸውን፡ ያለውልውል፡ በቍርጥ ታማኝነት ለመፈጸም፡ ምንጊዜም፡ ፍጹም ዝግጁዎች ኾነን የምንጠባበቅ፡ ትሑታንና ታዛዦች ካህናት መኾናችን የታወቀ ነው፤ በዚህ ረገድ፡ አኹንም፡ በእኔ በኩል፡ ምንም ዓይነት ችግር የለምና፡ ኹሉም፡ እነርሱ በወሰኑት ጊዜ እንደሚፈጸም ላረጋግጥልዎ፥ ሌሎቻችንም፡ ይኸው፡ "የኢትዮጵያ ቀን" የተባለው፡ እግዚአብሔራዊ ጊዜ እስኪደርስ፡ በትዕግሥት መጠባበቅ እንዳለብን፡ ላዘክርዎ እወድዳለሁ።  
በያለንበት፡ መልካም ጾመ ማርያም ይኹንልን!
ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፣
ላእከ ኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።