መንፈስ ቅዱስ፥ አጼ፥ አጼዪት፥ ሥዩመ-እግዚአብሔር፥ ሥይምተ-እግዚአብሔር፥ አጼ ቴዎድሮስ፥ እግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ:: መጋቢት ፭ ቀን፡ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (14th March 2017)

ከኪዳናዊ ዮሓንስ ደጉ፡ ስለአጼ ቴዎድሮስ ለቀረበ መጠይቃዊ አስተያየት የተሰጠ ምላሽ።

በቅዱሱ ኪዳን፡ መለኮታዊና ቋሚ የሥነ-ፍጥረት ሥርዓት እንደተደነገገው፡ "የኢትዮጵያ ልጆች" በተባሉት፡ በእግዚአብሔር ሕዝብ ዘንድ፡ የእግዚአብሔር ተጠሪ ኾኖ/ኾና ለማገልገል፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ባደረባቸው፡ በየራሳቸው፡ በኪዳናውያንና በኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች ድምፅ፣ ወይም የዕጣ-ጽሑፍ፥ ወይም፡ እጅ በማንሣት፥ ወይም፡ በማኖር ተመርጦ የሚሾመው ኢትዮጵያዊ፡ "አጼ"፥ ወይም፤ ተመርጣ የምትሾመው ኢትዮጵያዊት፡ "አጼዪት"፣ በዘልማድም፡ "ንግሥት" ይባላሉ።