ሥርዓተ-ተክሊል፥ ቀዳሚ፥ አዳም፥ ሴትነት፥ ጾታ፥ መገነዝ፥ ገንዘብ፥ ከረጢት፥ እስራት። የካቲት ፳፯ ቀን፡ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (06 March 2017)

ከኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን የደረሰን እጦማርና ለዚያ እጦማር የተሰጠ ምላሽ።

በቅዱሱ ኪዳን ወንድማችንና የአገልግሎት ተባባሪያችን ከኾነው ኪዳናዊ ዮሴፍ ጥላኹን፡ ለቀረበልን ኹለት ተከታታይ ጥያቄዎች፡ ከኢትዩጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት የተሰጠውን ማብራሪያ ጽሑፍ: ለእድምተኞቻችን የሚጠቅም እንደሆነ በማመን፡ ጥያቄዎቹንና መልሶቹን በአንድ ሰንድ ውስጥ በማካተት፡ በኅዋ-ሰሌዳችን ላይ ለይፋ ምንባብ አቅርበንላችኋልና ተመልከቱት።