ርእሰ ዐውደ ዓመት: ዕንቍጣጣሽ: ኢትዮጵያዊነት: ኤዶም ገነት: ደቂቀ እግዚአብሔር: ዓመተ-ኪዳን: ፪ ጳጉሜ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (07 Sep. 2017)

የ፪ሺ፲ (፳፻፲) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡
ከዘመነ ማቴዎስ፡ ወደዘመነ ማርቆስ አሸጋግሮ፡
የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡
የ፯ሺ፭፻፲ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዐሥረ)ኛውን
ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል፣
እንዲሁም፡
የአዳምና የሔዋንን ልደት፥
የቅዱሱ ኪዳን፡ መነሻ የኾነው ሥርዓተ ጋብቻም
የተከሠተበትን ቀን ያካተተውን፡ የፍጥረትን መገኛ
፯ሺ፭፻፲ኛውን ዓመት በዓል፥
ደግሞም፡ 
የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያምን፡
የ፪ሺ፳፮ (የኹለት ሽህ ሃያ ስድስተ)ኛውን ዓመት
እና
የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን፡
የ፪ሺ፲ (የኹለት ሽህ ዐሠረ)ኛውን ዓመት፡
የልደታት በዓል
ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ፡ የ፪ሺ፲ (፳፻፲)
(ኹለት ሽህ ዐሥር፥ ወይም፡ ሃያ መቶ ዐሥር፥ ወይም፡ ዕሥራ ምእት ወዐሠርቱ) ዓመተ-ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣