ቅኔ፣ መወድስ። ጥር ፲፰ ቀን፥ ፳፻፯ ዓ.ም. (January 27/01/2015)

ከመርዓዊ ጐሹ የደረስን ቅኔያዊ መልእክትና ለዚያ የተሰጠ ምላሽ።

ከመርዓዊ ጐሹ የተላከ።

ንቡረ፡እድ፡ኤርሚያስ፡ የሚከተለውን፡ቅኔ፡በጉባኤ፡ላይ፡አቅርቤው፡ነበር፡፡ያሎትን፡አስተያየት፡ቢሰጡኝ

መወድስ
ስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ
ፈጠሩ፡ሔዋን፡ወአዳም፡ይፈጥሩ
ዘዘነጽራዎ፡ዓይነ፡ይሄጽሩ
ዘዘኦዱ፡ዘዘኦዱ፡ዘዘኦዱ፡ዘዘየአውዱ፡ዘዘኦዱ፡ሠምሩ
አብርሃም፡ወይስሐቅ፡ሙሴ፡ወአሮን፡ፍና፡ኃቅለ፡ሲና፡ይትባደሩ
አበው፡እስራኤል፡ይትናገሩ
ሄሱ፡አርዮስ፡ወንብረ፡እድ፡(ኤርሚያስ)፡ይጻረሩ
ሊቀ፡ነቢያት፡ኤልያስ፡እብነ፡ሥላሴ፡ይዌሩ
ለዕለተ፡ሰንበት፡ፀላኢሃ፡አርዌ፡ገዳማት፡ከመ፡ይገሩ
ሊቀ፡ነቢያት፡ኤልያስ፡እብነ፡ሥላሴ፡ይዌሩ፡፡

ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ የተሰጠ ምላሽ።