ቍጥር ፯/፳፻፯ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ የወሊድ ቍጥጥር የሕዝብ ምጣኔ ፅንስ ማስወረድ የወንድ ዘር የወር አበባ:: መጋቢት ፲፮ ቀን፥ ፳፻፯ ዓመተ ምሕረት (25 March 2015)

ቍጥር ፯/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

የወሊድ ቍጥጥርን በተመለከተ።
የወሊድ ቍጥጥርን ከቶ ምንድር ነው? የእግዚአብሔር፥ ከእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ነወይ?

በዚህ አዋጅ የማሰማችሁ ቃሌ፡ ‘የወሊድ ቍጥጥር›› ተብሎ፡ ከአሕዛቡ ዓለም መንጭቶ፡ ‹ሕዝብ› በተባላችሁት የፈጣሪ ወገኖች ዘንድ፥ በተለይም፡ ‹ክርስቲያን ነን›፣ ‹ቤተ ክርስቲያንም ነን›፣ ይልቁንም፡ ‹ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ነን› በምትሉት ልጆቼ ዘንድ ሳይቀር፡ ተስፋፍቶ ስለተሠራጨው፡ ሰብኣዊና ባዕድ ስለኾነው የኑሮ ፈሊጥ፡ በኪዳናውያንና በኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች በኩል፡ እየቀረበ ላለው ጥያቄ፡ መልስ የኾነውን መለኮታዊ ሥርዓት የያዘው መልእክት ነው።