ዓቢይ ጾም፥ ሑዳዴ፥ ታላቁ ጾም፥ ሕዝባዊ ጾም፥ ምጽዋት፥ ስግደት፥ የካቲት ፩ ቀን፥ ፳፻፱ ዓ.ም. (08 February 2017)

ዓቢይ ጾም – ሑዳዴ።

የ፳፻፱ቱ (የሃያ መቶ ዘጠኙ=የኹለት ሺ ዘጠኙ) ዓመተ ምሕረት።

ይኸውም፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፥ በፍጥረታተ-ዓለማቷም ላይ ሊፈጽም፡ የክፋትና የሓሰት፥ የጥፋትና የሞት አባት የኾነው ዲያብሎስ፡ ከነጭፍሮቹ፡ አሢሮ የቀፈቀፈውንና ሲያካኼድ የኖረውን፥ አኹንም እያካኼደ ያለውን፡ የመንፈስና የነፍስ፥ የሥጋና የኹለንተና ጦርነት...