ፍልሰታሃ ለማርያም: ፍልሰት: ጌቴሴማኒ: ታውፋንያ: ዕፀ ሕይወት: አስተርእዮ: መጐናጸፊያ: ፲፬ ነሐሴ ፪ሺ፰ ዓ.ም (21 August 2016)

ፍልሰታሃ ለማርያም! ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል።

አግሃደት ፍልሰታሃ፡ ማርያም ድንግል!
በከመ ትንሣኤ ወልዳ፡ ዘልዑል!
ድንግል ማርያም፡ ፍልሰቷን ገለጠች!
የልጇን ትንሣኤ፡ በእርሱ አስመሰለች!

ልዑል እግዚአብሔር፡ሃይማኖታችንና አገራችን፥ እናታችንና ንግሥታችን፡መድኃኒታችን እግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡ ከምድር ወደሰማያት የተመለሰችበትን፡ የፍልሰቷን በዓል፡ ዘንድሮም፡ በ፳፻፰ተኛው (ኹለት ሽህ፡ ስምንተኛው) ዓመተ-ምሕረት፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ እንኳን፡ በሰላም ለማክበር አበቃን!