ዐውደ-ፀሓይ

ኪዳናዊ አክሊለ-ጊዮርጊስ፡ ስለትክክለኛውና ስለእውነተኛው የምድር ቅርጽ በተመለከተ ለላከልን የእ-ጦማር ጥያቄ፡ የተሰጠ መልስ።

ከኪዳናዊ አክሊለ-ጊዮርጊስ፡ የደረሰን እጦማር፦

+ዮም ፍሥሓ ኮነ!
በእንተ ፍልሰታ፡ ውስተ አርያም!
ለእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያም!+

     ጤናውን ይስጥልኝ፣ በእግዚኣብሔር መንግሥት፣ ኪዳናውያትና ኪዳናውያን እኅቶቼና ወንድሞቼ! እንደምን ኣላችሁልኝ!?
     ቤተሰቤና እኔ፣ በቸሩ ፈጣሪ እርዳታ፣ በፍጹም መልካም ሕይወት እንገኛለን፤ ምስጋናችሁ ዛሬም ይድረሳቸውና።
በዚህች እ-ጦማሬ ላስተላልፍ የፈለግኁትን ኣስተያየትና የሃሳብ ጥቆማ- የኪዳናዊ ጋሽዬ ኤርሚያስ ከበደ ቃለ መጠይቅ ሥዕላዊ መጽሔትን በተመለከተ- ሥዕላዊ መጽሔቱን ስመለከት፡ ገና ከመነሻው ላይ በተመለከትኩት፣ እንደእኔ እምነት ግን ትክክለኛ ኣይደለም ብዬ በያዝኩት፣ የምንኖርባትን ዓለም ሥዕላዊ መግለጫ ወይም የቅርፅና ሕልውና ጉዳያን በተመለከተ ነው።