ለመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ትምህርት፡ የተሰጠ ማብራሪያ መልስ።

ይድረስ፦ ለኪዳናውያንና ለኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች!
በያላችሁበት!

ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ፤
የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያ አገልጋይ።

የመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙን፡ አንድ ትምህርት በሚመለከት።

መግለጫ

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ፡ "እኔ" የሚለው ተውላጠ ስም፡ ለእግዚአብሔር መንግሥት
ኢትዮጵያ አገልጋይ፡ ለንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ፥ "እኛ" የሚለው፡
ለኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፥ "እርሳቸው" የሚለውም፡ ለመልአከ
መንክራት ግርማ ወንድሙ የቆሙ ቃላት መኾናቸው ይታወቅ!