ለኪዳናዊ አንዱ-ዓለም ደብዳቤ የተሰጠ መልስ።

ዮም ፍሥሓ ኮነ!
በእንተ ተዝካረ-ጾሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ መሲሕ!

ይድረስ፦ በቅዱሱ ኪዳን ለተወደድኸው ወንድሜና የአገልግሎት ባልደረባዬ፡ ኪዳናዊ አንዱዓለም!

በተወደደችው እኅታችንና የክህነት ባልደረባችን፡ በኪዳናዊት ኂሩት አማካይነት የላክህልኝ፣ ደኅንነትህን ያበሠረኝና መልካካም ቃላትን፣ አማናዊዉንና ተአምራዊዉን ሕልምህንም የያዘው፡ የምሥራች እ-ጦማርህ ደረሰኝ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

በአንተ በኩል እየተላለፈ፡ ለእኔም የሚደርሰኝ፡ በእየጊዜው፡ ወደአንተ የሚመጣው መለኮታዊ መልእክት፡ ለአንተ ብቻ ሳይኾን፡ ለኹላችንም ኪዳናውያንና ኪዳናውያት ሃይማኖትና ምግባር፥ አምልኮና ሕይወት ማጽኛ እንዲኾን፡ ሰማያውያኑና ዘለዓለማውያኑ ወላጆቻችን፡ እግዚአብሔር አብ እና እግዝእተብሔር እም ድንግል ማርያም የሚልኩልን ስለኾነ...