ቍጥር ፪/፳፻፮ ዓ. ም. የአዋጅ ቃል።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

በአገልግሎት መካፈል እንፈልጋለን በማለት ለጠየቃችሁ::

"በኢትዮጵያ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፡ በአገልግሎት መካፈል እንፈልጋለን!" በማለት፡ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ፡ ደጋግማችሁ ለጠየቃችሁና በዚሁ ጥያቄያችሁ መሠረት፡ አኹንም እያገለገላችሁ ላላችሁት፡ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት፡ ይህ የአዋጅ ቃልና ጥሪ፡ ምላሽ እንደሚኾናችሁ እናምናለን።

እውቀቱና ሙያው፥ ችሎታውና የገንዘብ ዓቅሙ ያላችሁ ኹሉ፡ ለምሳሌ፡ ከዚህ በሚከተሉት ዘርፎች፡ በያላችሁበት ኾናችሁ፡ ልትፈጽሙት ይቻላችኋል፤ ይኸውም፦
፩፡ በኅዋ ሰሌዳችንና በፌስቡክ መድረካችን፥ በዩቱብ መስኮታችንና በሌሎች የኅዋ ገጾቻችን ላይ በሚወጡ የጽሑፍ፥ የድምፅና የሥዕል መልእክቶቻችን ዝግጅትና አቅርቦት በመካፈል፣
፪፡ በግእዝና በኢትዮጵያኛ (ዐማርኛ)፥ እንዲሁም፡ በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ መጽሓፎቻችንንና መልእክቶቻችንን፡ ወደየቋንቋው በመተርጐም፣
፫፡ እነዚህን መጽሓፎችና መልእክቶች፥ ሌሎችንም፡ በማኅተም በማራባትና በማሠራጨት፣
፬፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነትን እውቀትና ልዩ ልዩ ሙያዎች፥ ግእዝንና ቅኔን፥ ዜማንና ቅዱሳት መጻሕፍትን፥ ሥዕልንና እደ ጥበብን፥ የመሳሰሉትን ዕንቍ ቅርሶቻችንን ጠብቆና አሳውቆ ለማስፋፋት፡ በግእዝና በኢትዮጵያኛ፥ እንዲሁም፡ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች በማዘጋጀት፥
፭፡ እነዚህን ሕያዋን መዘክሮችና ውርሶች ለማሳወቅ የሚያስችሉ፡ የሕፃናትና የትልልቆች ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም፣
፮፡ የእነዚህ ቅርሶችና ውርሶች ሕያዋን መዛግብት የኾኑት፡ ምሁራንና ባለሙያዎች፡ የእውቀት ዘራቸውን ዘርተው፡ ለፍሬ ለማብቃት የሚችሉበትን ዕድል አመቻችቶ በማቅረብ፣
፯፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖችን ኑሮ ለማሻሻል፡ በተጀመሩ የልማት ዕቅዶች ውስጥ በመሳተፍ ይኾናል።
 
ይህን ጥሪዋን ሰምታችሁና ተቀብላችሁ፡ "እም የት!" ብላችኋት፡ የእናታችሁን ፈቃድ ለመፈጸም ከተዘጋጃችሁ፡ ልታበረክቱ የምትፈልጉት አገልግሎት፡ ምን ዓይነትና በምንስ መልክ እንደኾነ፡ መልሳችሁን፡ በእነዚሁ የኅዋ ሰሌዳችንና የፌስቡክ መድረካችን አድራሻዎቻችን ልትልኩልን ይቻላል።

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...