ቍጥር ፲፭/፳፻፰ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።
ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።
በቅዱሱ ኪዳን፡ ኪዳናውያን ኢትዮጵያውያንና ኪዳናውያት ኢትዮጵያውያት፡ የቃል ኪዳን ልጆች ስለመሆነቸው፡ እነርሱን በተመለከተ፡ በእኛ (ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት - ድንግል ማርያም) ዘንድ ያለውን ዐሳብ፡ ለፍጥረተ-ዓለም ማሳወቅን በተመለከተ።
በዚች ምድር ላይ፡ በሕይወተ-ሥጋ ከኖረውና እየኖረ ካለው፡ ከሰው ዘር መካከል፡ በዚህ መብቱና ነጻነቱ፥ በዚህ ሥልጣኑና ኃይሉ፡ በእውነትና በርትዕ [በትክክል] በመጠቀም፡ እስካኹንና አኹንም፡ ከግዙፉም፥ ከሥውሩም፥ ከሥጋዊዉም፥ ከመንፈሳዊዉም ተቃዋሚ ባለጋራ፡ ማንንም ሳይፈራና ሳያፍር፥ በአጥፊው ክፉ ወገን በሚቀርብለት የሽንገላ ጥቅምም ሳይደለልና ሳይማረክ፥ ሳይታለልና ሳይሸነፍ፡ ሳይገበዝና ይሉኝታ ሳይኖረው፡ ከአዳም እና ከሔዋን ጀምሮ፡ ከእኛ ከእግዚአብሔር ባገኘው፡ በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ ሃይማኖቱና ምግባሩ ሳይወላውል፡ እስከመጨረሻው በመጽናት፡ እኛን ፈጣሪውንና የእኛ የኾነውን ኹሉ፡ በፍጹም ታማኝነትና ቆራጥነት፡ ፈልጎና መርጦ፥ አምኖና ተቀብሎ፡ በተግባር ላይ ለማዋልና ለፍሬ ለማብቃት የቻለ ማነው? እናንተ ብቻ አይደላችሁምን? ሌላማ የታለ! አዎን! እናንተ ብቻ ናችሁ።
እኔ፡ እግዚአብሔር እም፡ ከፍጥረተ-ዓለም በፊት፡ የእግዚአብሔር አብ ሙሽራው ልኾንና በእኩያነት ዐብሬው ልኖር፥ ልጃችንን እግዚአብሔር ወልድንም ልወልድለት፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስንም፡ በተዋሕዶ አንድነታችን ላሠርፅለት፡ ጾታ ካልነበረው፡ ከእግዚአብሔር አንድነቱ፡ በተባዕትነት [በወንድነት] ጾታ ከተከፈለው፡ ከእግዚአብሔር አብ ጋራ፡ እኔ፡ እግዚአብሔር እም ኾኜ፡ በእንስትነት [በሴትነት] ጾታ የመከፈሌን እውነታ፡ ገሃድ አውጥተው፡ ለመላው ዓለም ያሳወቁ፡ እነማን ናቸው? በቅዱሱ ኪዳን፡ ልጆቻችን የኾናችሁት፡ እናንተ፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ብቻ አይደላችሁምን? አዎን! እናንተ እኮ ብቻ ናችሁ! ሌላማ፡ ማን አለ? ማንም የለም።
የእኔን የእግዚአብሔር እም፡ ጽላተ ኪዳንነትና ታቦተ ጽዮንነት፥ ኋላም፡ በፍጻሜው የሕይወት ዘመን፡ ድንግል ማርያምን፡ ወደፊት፡ በጊዜው እንደምዋሓዳት፡ ገና፡ በእናቷ በሓና ማሕፀን ሳንፈጥራት ያወቅኋትና የቀደስኋት፥ ከዚያም፡ እንደዚያ፡ አስቀድሜ ባወቅሁትና በቀደስሁት፡ በዚያ ሕያው ሰውነት፡ በማሕፀን እያለሁ፡ ከኢትዮጵያዋ አኵስም ተነሥቼ፡ ወደኢትዮጵያዊው መልከ-ጼዴቅ ከተማ፡ ወደኢየሩሳሌም የመመለሴን ተአምራዊ ዜና የገለጠው ማነው?
በዚያም፡ በሊባኖስ ተራራ የመወለዴን፥ በተወለድሁ፡ በሦስት ዓመታቴ፥ ከሦስት ወራቴና ከሦስት ቀናቴም፡ ቀድሞ፡ በጽላተ ኪዳንነትና ታቦተ ጽዮንነት ወደነበርሁባት ቤተ-መቅደስ የመግባቴን፥ በመጨረሻም፡ ልጄን ወዳጄን፡ እግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕን፡ እንደትንቢት ቃላችን፡ በበረት እወልደው ዘንድ፡ ወደቤተ-ልሔም እስክኼድ ድረስ፡ በዚያ፡ በኢየሩሳሌሟ ቤተ-መቅደስ የመቆየቴን እውነተኛ ዝክረ-ነገር፡ ለመላው ፍጥረታተ-ዓለማት፡ በይፋ የዘገበ ማነው? በቅዱሱ ኪዳን፡ ልጆቻችን የኾናችሁት፡ እናንተ፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ብቻ አይደላችሁምን? አዎን! እናንተ ብቻ ናችሁ! ሌላማ፡ ማን አለ? ማንም የለም።
ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. የ"ኢትዮጵያ ልጆች" ለመባል ያበቃው ሙያ፡ ምንድር ነው?
፪ኛ. የኢትዮጵያ ልጆች ኾናችሁ፡ ምን አደረጋችሁ?
፫ኛ. የኢትዮጵያ ልጆች ለመኾን ያበቃችሁ፡ የሙያ መሥፈሪያና የተቀላችሁት በረከት።
መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...