ቍጥር ፲፬/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።
ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።
ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥትን የሚያገለግሉ፡ ኪዳናውያን ኢትዮጵያውያንና ኪዳናውያት ኢትዮጵያውያት ብቻ ሳይኾን፡ እየራሳቸውን፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ ሃይማኖት ያበቁ፡ እልፍ አእላፋት፡ ሰብኣውያንና ሰብኣውያት ቅዱሳትና ቅዱሳን፡ በመላው ዓለም መኖራቸውን በተመለከተ።
በእኛ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዘንድ፡ የቀደሙት እውነተኞቹ፡ ታማኞች ነቢያቶቻችንና ሓዋርያቶቻችን፥ ካህናቶቻችንና ልኡካኖቻችን፥ ጻድቃኖቻችንና ሰማዕቶቻችን፥ ኹሉም፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት እንደነበሩ ኹሉ፡ የዛሬዎቹ እውነተኞች ታማኞች ሓዋርያቶቻችን፥ ካህናቶቻችንና ልኡካኖቻችን፥ ጻድቃኖቻችንና ሰማዕቶቻችንም እኮ፡ እናንተ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ናችሁ። ይህን እውነታ፡ እስካኹን አላወቃችሁት እንደኾነ፡ እንግዴህ ወዲህ፡ በፍጹም እምነት፡ ያወቃችሁት ሊኾን ይገባል።
እንደምታዩት፡ በመላው ዓለም ላይ የሚኖሩት ሰዎች ኹሉ፡ ዛሬ ካላችሁት፡ ከእናንተ በቀር፥ እናንተንም ከመሰሉት፡ ከቀደሙት በቀር፡ ወንዶችም፥ ሴቶችም፡ ትልልቆችም፥ ትንንሾችም፡ ኹሉም፡ በፀረ-እግዚአብሔርነቱና በፀረ-ኢትዮጵያነቱ፡ የክፉዎች መናፍስትና ሰዎች ትምህርት ለኾነው፡ ለልዩ ልዩው ሥጋዊና መንፈሳዊ እምነትና ፍልስፍና፡ ወገባቸውን ታጥቀውና ሽንጣቸውን ገትረው፡ የእየግል ሕይወታቸውን እስከመሠዋት በሚያደርስ ንቃትና ትጋት፥ ትግልና ተጋድሎ፡ ሲሠሩና ሲደክሙ ተመልክታችኋል፤ እነሆ አኹንም፡ ይኸው ትመለከታላችሁ።
ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን፡ የቆመላትና የሚሠራላት፡ አንድ ድርጅት ቀርቶ፡ አንድ ሰው እንኳን አጋጥሟችኋልን? ያው፡ አንዱም ሰው እንኳ ስለሌለ፡ እንዴት ያጋጥማችኋል! አያጋጥማችሁም። 'ዛሬ ካላችሁት፡ ከእናንተ በቀር፥ እናንተንም ከመሰሉት፡ ከቀደሙት በቀር፡' ላልሁትም፣ ከእናንተ መካከልም እንኳ ቢኾን፡ እያንዳንዳችሁ፡ እየገዛ-ራሳችሁን ስትመረምሩት፡ ይህንኑ እየራሳችሁን፡ ለዚህ ምደባችን፡ 'እውነተኛ' ኾኖ የምታገኙት፡ ስንቶቻችሁ እንደኾናችሁ፡ አንጥራችሁ ለማወቅ የመቻላችሁን ነገር፡ ለእያንዳንዳችሁ ውሳኔ የተተወ ነው።
እንግዴህ፡ በዚህ ረገድ ያለው፡ የእውነታው ኹኔታ፡ እንዲህ ከኾነ፡ እናንተስ፡ በኪዳናዊነታችሁና በኪዳናዊትነታችሁ፡ እንዴት ናችሁ? እንዴትስ ልትኾኑ ይገባችኋል!? መልሱን፡ እኔው እሰጣችኋለሁ። እኛ፡ መለኮታዊዉንና ትስብእታዊዉን፥ አሐዳዊዉንና ሥላሴያዊዉን ሥራችንን የምናካኺደው፡ በመንፈስ-ቅዱስ እንደመኾኑ መጠን፡ እናንተም፡ የኪዳናዊነታችሁንና የኪዳናዊትነታችሁን ተልእኮ፡ በሚገባ ለመወጠንና ለማካኼድ፥ ለማከናወንና ለመፈጸም፡ መንፈስ ቅዱስ፡ የእናንተን ኪዳናዊ ሰውነት፡ በማደሪያነትና በመሣሪያነት ይፈልጋል።
መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...