በፌስ-ቡክ መድረካችን ላይ በሰኔ ወር፥ ፳፻፰ ዓ. ም. ለቀረቡ ጥያቄዎችና ትችቶች፡ ከኢእመ የተሰጡ መልሶች። ፫ኛ።

ከWondish Leul የተሠነዘረ የነቀፋና የዘለፋ ትች፦

     AYYyyyyy tiliku sewuye leka eskahun mishig yizeh yihen yekihidet kal eyezerah new ENAT BETEKRSTIANIN eyasedebkina yalhonechiwun yalastemarechiwun endebedelina kifu timhirt kotrew leloch afachewun endikeftu yemtadergewu. Baynekabih noro gud
serteh neber ahun gin maninetihina sirah siletenekabih kezih behuala maninim atatalilim!!!!!!!!!!!!

የኢእመ መልስ፦

ይድረስ፦ ለወይዘሪት/ወይዘሮ ወንድሽ ልዑል!
     ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን፡ በእግዚአብሔር ስም እያቀረብንልዎ፡ በፌስ-ቡክ ኅዋ መድረካችን ላይ ስለሠነዘሩት የነቀፋና የዘለፋ ትች፡ የምንሰጥዎ መልስ፡ "እግዜር ይስጥልን!" ከሚለው አጻፋችን ጋር፡ ባጭሩ፡ ከዚህ የሚከተለው ነው።
     እርስዎ፡ "እናት ቤተ-ክርስቲያን" የሚሏት፡ የትኛዋን ነው? የእርስዎን? ወይስ፡ የእኛን? ወይስ፡ የዛሬ ፫ሺ፰ ዓመታት፡ በኦሪታውያኑ አይሁድ የቅኝ ቀንበር ሥር ወድቃ፡ እየማቀቀች ያለችውን፥ ደግሞም፡ የዛሬ ፩ሺ፮፻፰ ዓመታት፡ በ፬ኛው የክርስትና ምእት-ዓመት ላይ፡ በግብፃውያን መነኮሳት፡ በኢትዮጵያ ምድር እንደተቋቋመች፡ ራሷ አምና፡ ሌሎችንም ለማሳመን የምትጥረውን፣ ራሷንም፡ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን!" ብላ የምትጠራውን ነወይ፡ እርስዎ፡ "እናት ቤተ- ክርስቲያን" የሚሏት?

የጥያቄና መልሱን ሙሉ ክንውን ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...