''አሳዛኝ ቃል'' በሚል አርእስት፡ ከአባ ወልደ-አረጋዊ (አባ ዳንኤል ተጫኔ)፡ ለኹለተኛ ጊዜ፡ የተላከ መልእክት።

አሳዛኝ ቃል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ይትባረክ አምላከ አበዊነ ይድረስ ለንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ 

ንጉሥ ቴዎድሮስ ዘኢትዮ ለሚለው ጽሁፍ የሰጡት ምላሽ ልብ የሚሰብር እውነትን አጉልቶ ያላሳየ የተድበሰበሰ ነው ሌላው ለእርስዎ ተጽፎ የደረሰዎት ከመልእክቱ እዳየሁት ህዳር 14 1995 እስከዛሬ መልስ ሳይሰጡበት ቀርው ነው ወይስ ፊት የሰጡት መልስ ነው ከሆነስ አሁን እደገና ይህን ሀሳብ ለምን ማሳት ፈለጉ አላማው ምድነው አበው በትንቢት ያስቀመጡትን እውነት ደጉ ንጉሥ ቴዎድሮስ መገለጥ ብዙ ጊዜ ይቃወማሉ ደግሞም በቂ ማብራሪያ የለዎትም ለመሆኑ ማነው ይህን እውነት የሚከድነው ይህ የመለኮት ቃልና ፈቃድ ሆኖ ሳለ ማነው ሊሸፍነው የሚቻለው ኢትዮጵያዊነትን በአለም የሚያነግስ ቴዎድሮስ አለምን አንድ የሚያደርግ ቴዎድሮስ ከአንድ በሬ እሸት ከአንድ ላም ወተት ዘመን የሚከስት ቴዎድሮስ አውሬውን የሚያስር የዘመናትን ደባ የሚገላልጥ ቴዎድሮስ ንጹሐን ኢትዮጵያውያን ገዳማውያን በዋሻ በፍርኩታ ጤዛ ልሰው ድጋይ ተተርሰው ቅጠል በጥሰው ለዘመናት ተሰውረው የሚኖሩ አበው የሚጠብቁት ቴዎድሮስ ተሰውሮ ያለው ቴዎድሮስ ዘመኑ ሰአቱ ሲደርስ ስለኢትዮጵያ ከመለኮት መንበር ተቀብቶ የሚመጣው የሚገለጠው ቴዎድሮስ ስለዚህ መናገርና እውነቱ ይህነው እናተ በስሙ በየጊዜው የምትበቅሉ አረሞች ግን አቁሙ ከስተታችሁ ተመለሱ አማናዊውን ቴዎድሮስ ደጉን ቀናኢውን ቴዎድሮስ ለዘመናት ተሰውሮ በአበው ልቦና ያለውን ቴዎድሮስ ዘመን እድታዩ አምላከ ኢትዮጵያን ለምኑ ወዳጆቸ ኢትዮጵያውያንም በሰው ፈቃድ ሳይሆን በመለኮት ጊዜና ሰዓት በሃይልና በስልጣን ከቅድሳን ስውራን ጋር የሚገለውን ደግ አባት ደግ ዘመን ጠብቁ ብለው ለምን አላሉም ወይስ አምላካዊ የሆነውን እውነት እኛ ስላልተናገርን የሚቀር አድርገን ወሰን ዛሬ የጠፋውን ኢትዮጵያዊነት የሚመለረስ ደጉ ቴዎድሮስ አለምን አንድ የሚያደርገው ቴዎድሮስ ሰላሙን ዘመን የሚከስተው ቴዎድሮስ እንዳበሳ እያገሳ አለምን(አማጽያንን) በብረት ዘንግ የሚቀጠቅጣቸው ቴዎድሮስ በመጨረሻም አለም አንድ ሆኖ ሁሉን አንድ አድርጎ የኢትዮጵያዊነት ተዋህዶ ሀይማኖት ሰንበት እረፍት በአለም የሚያሰፍነው ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ የአለሙ መፋረጃ የመለኮት የፍርድ ምድርነቷን የሚገልጠው ቴዎድሮስ ተገልጦአል ይህን እውነት ለመድፈን ደፋ ቀና ከሚሉት ጉን መሰለፍዎ ደግሞ እጅጉን ያሳዝናል ከእደርሶ አይነት አባት የሚጠበቀው ፍሬ ይህ አልነበረም ወደድንም ጠላን ግን ሁላችንም ከእጁ አናመልጥም ሁሉ በሱ ያላፋል እሱስ የማንም ድጋፍ አያስፈልገው የሚሰራውን የሚያውቅ ሁሉ ለሥላሴ የተሰጠው ሃያል ባለስልጣን በቃሉ ተፈጥሮን ማዘዝ የሚችል አንድ ሰው ቅዱሳንን ሁሉ በጉኑ ያሰለፈ መሆኑን ይገዘቡ የኒቆዶሞስን እድል ያድልዎ ሌላው አብይ ጉዳይ ግልባጭ ለአለቃ አያሌው ታምሩ የሚለው ነው ፍየል ወዲያ ቅምዝምዝ ወዲህ እዲሉ አበው የሆነው ይኸው ነው ደጉ አባት አለም በክህደት ሲሰጥም ቤተክርስቲያን የመናፍቃን ዋሻ በሆነችበት ሰአት ብቻቸውን እለተዋህዶ የቀኑ እቢ ለሀይማኖቴ ሀገሬ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ ባላስብሽ ምላሴ ከትናጋየ ይጣበቅ ብለው አገቴን ለሰይፍ ተዋህዶን ኢትዮጵያን አላስደፍርም ብለው ብቻቸውን የቆሙ ቆመውም ያሳዩ ሰማእት የሚያውቁትን ቴዎድሮስ እደማያውቁት አድርጎ መዳፍ ነካሽ ባንዳ ቴዎድሮስ እኔነኝ ማለት ምናይነት ድፈረት ነው አቅምን አለማወቅ በእረፍታቸው ቅጽበት አባታችን ለመጨረሻ ጊዜ ሳይሰናበቱን ውግዘትዎትን ያሱልን ተብለው ሲጠየቁ እኔ ብፈታው መለኮት አይፈታውም እኔ በራሴ ያደረኩት የለም የመለኮትን ፈርድ ጠብቁ ሰአቱ ደርሶአል ታገሱ ሁሉን የሚፈታው ሁሉን የሚገልጠው ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣላችሁዋል እስከዛ በቃሌ ጽኑ ከአማጽን ከመናፍቃን እዳትደመሩ ያሉትን ቃላቸውን አስቡ ደጉ ቅዱሱ እውነት በጠፋበት ስለእውነት የቆሙት አለዋ አያሌው ታምሩ ቴዎድሮስን ጠቅቀው ያውቁታል ይልቅ እኛ አባታችንን እንወቃቸው ለእውነት ስለእውነት እቁም ወስበሐት ለእግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ወልድ ዋህድ እትዮጵያ ሀገረ ማርያም እመ ፍጥረት እግዚአብሔር ወልድ ዋህድ የተዋሕዶ አንበሳ ማርያም እመፍጥረት የተዋሕዶ ጣእዋ ኢትዮጵያ ተነስታለች አንበሳው አግስቶአል ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ለሚከናወነው የአለማችን መጥፋትም ሆነ መዳን የመለኮት የፍርድ ምድር

ከኢእመ የተሰጠ መልስ፦ 

''ንጉሥ ቴዎድሮስ ነኝ'' ላለው ግለሰብ፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት፡ የሰጠነውን ምላሽ፡ የያዘው ሰነድ፦