እስእለኪ ማርያም በሃሌ ሉያ!

የግራኝ አሕመድ ጦር በተቃጣበት፡ በዐጤ ልብነ ድንግል ዘመን፡ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ያቀረቡት፡ የምሕላ ጸሎት!

በግእዝ፦

በእንተ ፍቅረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኬንያ፡
እስእለኪ ማርያም በሃሌ ሉያ!
ኀዘና ስምዒ ወብካያ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ።

በኢትዮጵያኛ፦

ሠሪዋ በኾነው፡ በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር ኾነሽ፥
ማርያም ሆይ! በሃሌ ሉያ፡ የምስጋና ቃል የምንለምንሽ፥
አገራችን ኢትዮጵያን፡ ኀዘኗንና ለቅሶዋን ሰምተሽ፥
እንድታማልጂ ነው ከልጅሽ።