ከአቶ አንዋር አሕመድ የቀረበ ጥያቄና ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግስት፡ የተሰጠ መልስ።

ከአቶ አንዋር አሕመድ የቀረበ ጥያቄ፦

1+1+1 =______ ስንት ነው፡ ለክርስቲያኖች?
 

ከኢእመ የተሰጠ መልስ፦

ይድረስ፦ ለአቶ አንዋር አሕመድ!

ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን፡ በእግዚአብሔር ስም እናቀርብልዎታለን። ከዚህ በላይ ላቀረቡት ጥያቄ፡ እንደሚከተለው፡ ተገቢውን መልስ እናበረክትዎታለን፤ የምናበረክትዎትም፡ ከሥጋዊው ይልቅ፡ በመንፈሳዊው የተፈጥሮ አእምሮዎ ተጠቅመው እንደሚረዱት በማመን ነው። ሰዎች፡ የጻፏቸውን መጽሓፍ ቅዱስን፥ ወይም፡ ቍርዓንን እየጠቀሱ በመከራከር፡ እውነተኛዋ ሃይማኖት አትገኝም። እርስዎና እኛ፡ ሰዎች በፈጠሯቸው እምነቶች ሳይኾን፡ ከእውነተኛዋ የእግዚአብሔር ሃይማኖት ለመድረስ እና እርሷን ለማወቅ የምንችለው፡ በንጹሕ ሰብኣዊ ፍቅር ኾነን፡ በመግባባትና እግዚአብሔር፡ በተፈጥሮአችን፡ በውስጣችን ባኖረው የእውቀት ኃይል፡ በእርጋታ ስንነጋገር ብቻ ነው።