ከኪዳናዊ አንዱ-ዓለም የደረሰን ደብዳቤ።

ይድረስ፦ ለተወደድከው ኪዳናዊው ጋሽዬ፡ በያለንበት በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፡ ቸሪቱንና ደጊቱን፡ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥትን፡ ከነልጅዋ ከመድሃኒዓለም ጋር እያመሰገንሁ፡ ኪዳናዊ የወንድምነት ሰላምታዬን፡ ለኪዳናዊው ቤተሰብህ ጭምር አቀርብልሃለሁ።
በመቀጠልም፡ ከዚህ በፊት የምሥራች እንደምልህ ሁሉ፡ ዛሬም በዕለተ መድሃኒዓለም የምሥራች ልልህ እወዳለሁ።

በ፳፬/፫/፳፻፱ ዓ.ም. በዕለተ ቅዳሜ ያየሁት ሕልም ነው።

የማላውቃቸው ሰዎች እኔን በሆነ ምክንያት ሊከስሱኝና ሊያስፈርዱብኝ ፈልገው፡ በአንድ የፍርድ አደባባይ ላይ፡ ዙሪያዬን ከብበው ያቆሙኝ ይመስለኛል። ዳኛዋ ደግሞ ሴት ናት፤ ከሴትም ትልቅ ሴት ናት ("አሮጊት ሴት" ብለን እንደምንጠራት አይነት ሴት ማለት ናት)።
በመጨረሻም ይህቺ ዳኛይቱ ሴት ለከሳሾቼ፦ "ለእኔ ግን፡ ኹሉም ሰው፡ አንዱዓለም የለበሰውን ልብስ ቢለብሱ ጥሩ ነው" አለቻቸው።
ከሳሾቼም ወደእኔ ተሰብስበው መጡና፦ "ያንተ ልብስ ምንድን ነው?" ብለው ጠየቁኝ።

እኔም፦ "የእኔ ልብስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ያውም ኢትዮጵያዊነቱ!" በማለት መለስኩላቸው።
እንግዲህ ጋሽዬ፡ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት የምታስተምረውን እውነት፡ በሕልሜ ስትመሠክርልኝ ከመስማትና ከማዬት በቀር፡ ሌላ የምሥራች ምን አለ?

አንዱ-ዓለም