"የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች!" ለሚለው የትችት ሐተታ፣ ከሃይለ መለኮት: በሚል አድራሻና የጸሓፊ ስም፡ የተሰጠ የመልስ ሓተታ::

"የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች!"  ክፍል አንድ እና ክፍል ኹለት" በሚል አርእስት፡ "በመስከረም ፳፻፰ ዓ. ም. ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቀረበና ለዓለም የተሠራጨ መልእክት" ለሚለው የትችት ሐተታ፣

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ!" በሚል መክፈቻ፡ "ጥቅምት ፫ ቀን÷ ፳፻፰ ዓ. ም. ይድረስ ፡ ለውድ ወንድሜ ዲ. ዳንኤል ክብረት! ከሃይለ መለኮት፦" በሚል አድራሻና የጸሓፊ ስም፡ የተሰጠውን የመልስ ሓተታ፥ ለአንባቢዎቻችን እንድትመለከቷቸው፡ ይኸው አቅርበንላችኋል።

መልስ ሰጪው፡ ኃይለ-መለኮትም፡ በመለኮት ኃይል ተመርተው፡ ለሰጡት ምላሽ፥ እኛም፡ ይህንኑ መልሳቸውን፡ በግልባጭ እንድናውቀው በማድረጋቸው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ስም፡ "የእግዚአብሔር ይስጥልን!" ምርቃታችንን፡ በዚሁ የመልሳችን ቅጂ አማካይነት፡ ይኸው ከመንፈስ ቅዱስ ሰላምታችንና አድናቆታችን ጋር ልከንላቸዋል።