የ፪ሺ፲፬ (፳፻፲፬) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።
Submitted by etkog12 on Fri, 09/10/2021 - 07:51
ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ማቴዎስ፡ ወደዘመነ ማርቆስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡
የ፯ሺ፭፻፲፬ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዐሥራአራተ) ኛውን ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል፣
እንዲሁም፡
የአዳምና የሔዋንን ልደት፥ የቅዱሱ ኪዳን፡ መነሻ የኾነው ሥርዓተ ጋብቻም የተከሠተበትን ቀን ያካተተውን፡ የፍጥረትን መገኛ ፯ሺ፭፻፲፬ኛውን ዓመት በዓል፥
ደግሞም፡ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያምን፡ የ፪ሺ፴ (የኹለት ሽህ ሰላሳ)ኛውን ዓመት
እና
የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን፡ የ፪ሺ፲፬ (የኹለት ሽህ ዐሠራአራት)ኛውን ዓመት፡ የልደታት በዓል
ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ፡ የ፪ሺ፲፬ (፳፻፲፬) (ኹለት ሽህ ዐሥራአራት፥ ወይም፡ ሃያ መቶ ዐሥራአራት፥ ወይም፡ ዕሥራ ምእት ወዐሠርተዐርባእቱ) ዓመተ-ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣ እንኳን፡ በያለንበት፡ በሰላም አደረሰን!
መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...