ቅዱሱ ኪዳን፡ "የወሊድ መቆጣጠር"ን ሲገመግም።

ከአክሊለ ጊዬርጊስ የቀረበ ጥያቄ፦

    ጋሽዬ ንቡረ እድ ኤርሚያስ ከ.፣ "ጤናውን ይስጥልኝ!" እያልኩ ሰላምታዬን አቀርባለው፡፡
    እኔ፣ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ቅድስት እናቱ እናታችን ማርያም፣ ቅዱስ መስቀላቸውም፡ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ምንጊዜም የተከበሩና የተመሰገኑ ይኹኑልን፣ እጅጉን ደኅና ነኝ! ትንሽ ጥያቄ ስላለችኝ፡ እባክዎን እንዲህ ላቅርባት? እግዜር ይስጥልኝ፡፡
    አንደኛ ጥያቄ፡- 
    ከ፲ቱ ትእዛዛተ እግዚአብሔር፡ አንዱ ስለኾነው፡ የሰንበት ቀን አከባበር በተመለከተ፤ በተለምዶ፡ በአገራችን የሚታየውን አከባበር በጥሞና ስመለከተው፡ በሰንበት መደረግ እና/ወይም አለመደረግ ያለበት የቱና የቱ ተግባር/ሥራ ነው? የሚለው እጅጉን አሳስቦኛል፤ እስከአሁንም በግልጽ አልተረዳሁትም፡፡ ምክንያቱም፡ ወጣ ያሉና አሁንም እንደኦሪቱ ሸክም የኾኑ ተግባሮች ሲደረጉ የሚታዩ እየመሰለኝ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ፡ ለምሳሌ፡- እንደጾም እና በዓል ቀን ሁሉ፡ የባለቃልኪዳን ባለትዳሮች ምንጣፍ፡ በሰንበት ይከለከላልን? (በመሠረቱ፡ የቃልኪዳን ባለትዳሮችን ምንጣፍ በተመለከተ፡ ብዙ የተዛቡና የሐሰት ግንዛቤዎች በትውልዱ ዘንድ እንዳሉ ልብ ይሏል፤)በቅዱስ መጽሓፍ፡ በሰንበት ዕለት፡ ሸክም ወደከተማችን እንዳናስገባና እንዳናወጣ፤ ሥራንም ጭምር እንዳንሠራበት ያዝዘናልና፡ ይህን ትእዛዝ እንዴት በጠራ መልኩ ተረድተን ነው ልንፈጽመው የሚገባን? 
    በአጠቃላይ፡ እንደቅዱሳት መጻሕፍቱ ምስክርነት፡ በተለይ፡ በአዲስ ኪዳን የኪዳነ ምሕረት የጸጋ ዘመን ለምንገኝ፡ ለእኛ፡ በትክክለኛው የእውነትና የመንፈስ አምልኮ ኾነን ልናከብረው ስለሚገባን፡ የሰንበት አከባበር፡ እባክዎ ካህን፡ በማስረዳት ቢያገለግሉኝ?
    ኹለተኛ ጥያቄ፡-
    የወሊድ መቆጣጠሪያ ተብሎ፡ ከአሕዛቡ ዓለም መንጭቶ የተሠራጨው ፡ ሕዝብ የተባሉት፡ የፈጣሪ ወገኖች፡ ክርስቲያን ነን፣ ቤተ ክርስቲያን ነን፡፡ የሚሉት ሳይቀሩ፣ በተለይ፡ ኢትዮጵያውያን/ት ነን፡፡ የምንለው፡ ያለፉት ሦስትና ኹለት ትውልድ፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፡ ከሕዝቡ ምሉካንና ከእምነት ተቋሞቻችን ጋር በአንድነት፡ ምንም ዓይነት የጠራ አቋም ሳይያዝ፡ አፋቸውን እንደሚለጉሟቸው እንስሶች፡ እንዲህ በዝምታ፡ ሳናወላውልና በይፋ ሳንመክርበት ስለምንተገብረው ሰው ሠራሽ ዘዴ የወሊድ መቆጣጠሪያ መሣሪያ፡ እንደቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያ ትምህርት፡ እውነተኞች የፈጣሪ ወገኞች፡ ከዚህ አኳያ ያላቸው መረዳትና አቋም፡ እንዴት ያለ ነው? በተለይ፡ አሁን ያለነው ትውልድ፡ እድላችን ኾኖ በተወዛገበ የሕይወት አካሄድ ላይ ስለምንገኝ፡ እባክዎ እውነታውን በመንገር ቢያገለግሉን? እግዜር ይስጥልኝ!
+አጊወመ+

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ የተሰጠ መልስ፦ 

ለኪዳናዊ ወንድሜና የአገልግሎት ባልደረባዬ አክሊለ ጊዮርጊስ!

    ሙሉ ደኅንነትህን፡ ከጦማርህ በማወቄ፡ ደስ ብሎኝ፣ እኔም፡ በኹለንተናዊ ጤንነት ላይ ስለምገኝ፡ ለፈጣሪዬ፥ ለቅድስት እናቱም፡ የምስጋና ቍርባንን እያቀረብሁ አለሁ።
    ወደዋናው የመልስ ጽሑፌ ከመግባቴ በፊት፡ በጦማርህ ውስጥ ስላገኘሁት፡ አንዲት ነገር፡ የምልህ አለኝ፤ እርሱም፡ "ኪዳናዊ ወንድምህ መኾኔን፡ በሃይማኖት ተቀብለህ፡ "ጋሽዬ!" ብለህ፡ በእግዚአብሔር እውነት ካቀረብኸኝ በኋላ፡ ምነው ታዲያ፡ "እባክዎ!" በሚለው፡ በተቃራኒው የአንቱታ ግብዝነት አራቅኸኝ!?" በሚል ቃል ልገልጽልህ የፈለግሁት ትችቴ ነው።
    ይኼ ዓይነቱ የለብታ አቋምና አካኼድማ፡ በእኛ በእውነተኞች ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች ዘንድ፡ ፈጽሞ ቦታ ሊኖ ረው አይገባም፤ ስለዚህ፡ ይኸው ተፃራሪ ድርጊት፡ ለወደፊቱ፡ በማንኛችንም በኩል እንደማይደገም አምናለሁ። (ራእ. ፫፥ ፲፭-፳፪።) 
    "ኤርሚያስ" የሚለውም፡ የአጻጻፍ ስሕተት፡ "ኤርምያስ" በሚለው ሆሄ ይስተካከል ዘንድ፡ እርማቱን፡ በትሕትና አቅርቤአለሁ።
    ይህን ካልሁ በኋላ፡ ዓቢይ ስለኾነው፡ ስለጥያቄዎችህ ቍም ነገር፡ ያለኝን መልስ ወደመስጠቱና ከዚህ የተነሣ የተላለፈውን ልዩ መልእክት ወደማቅረቡ እኼዳለሁ።