ስለአዲሱ የኅዋ ሰሌዳችን አገልግሎት።
ይህ የምትመለከቱት፡ አዲሱ የኅዋ ሰሌዳ፡ በተለያዩ፡ እንደጭን መቀመሪያና የኪስ ስልክ ባሉ፡ የኅዋ ዐውታር አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ላይ፡ ብቅዓትና ጥራት ባለው መልኩ፡ አገልግሎት እንዲሰጥ፥ እንዲሁም፡ በተለያዩ፡ የኅዋ ዐውታር መጐብኛዎችም ላይ፡ ኢትዮጵያኛ (ዐምሓርኛ)ውን ሆሄያት፡ ያለምንም ችግር፡ ለቅሞና አጣርቶ ማንበብ እንዲያስችል ተደርጐ፡ በዘመናዊ መልኩ የተዘጋጀና የተዋቀረ ነው።
ይህ የኅዋ ሰሌዳ፡ እንደመጀመሪያውና እንደነባሩ ኹሉ፦ «ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኗን፥ ኢትዮጵያውያንም፡ የቅዱሱ ኪዳን ሕዝብ መኾናቸውን ለማስረዳት፥ የ"ኢትዮጵያ" እና የ"ኢትዮጵያውያን" የኾነውንም ኹሉ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ» ለሚል፡ መለኮታዊ ዓላማ የሚውል ሲኾን፥ ይህ የኅዋ ሰሌዳ፡ በተለይ፡ በድምፅና በሥዕል የሚተላለፉትን መልእክቶች፡ ቀላል በኾነ መልክና ዘዴ፡ ለመስማትና ለመመልከት እንዲያስችል ተደርጐ የተዘጋጀ መኾኑን እናምናለን።
ወደፊት፡ በመደበኛነት ከምንጠቀምባቸው፡ ከግእዝ፥ ከኢትዮጵያኛና ከእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ባሻገር፡ የዚህን፡ የኅዋ ሰሌዳ ይዘትና የምናስተላልፋቸውን መልእክቶች፡ ወደተለያዩ አገሮች ቋንቋ በመተርጐም፡ የምናቀርብ መኾኑን፡ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወድዳለን። ለዚህ ዓላማ መሳካት፡ በቍጥር ፪/፳፻፮ ዓ. ም. ባስተላለፍነው የነጋሪት ቃል መሠረት፡ ከእኛ ጋር ለመሥራት የምትፈልጉ ካላችሁ፡ እናንት፡ ኪዳናውያትና ኪዳናውያን፡ ያን ልታሳውቁን ትችላላችሁ።
«ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኗንና ኢትዮጵያውያትና ኢትዮጵያውያንም፡ የእግዚአብሔር ልጆች የመኾናቸውን» እውነታ፡ ለዓለሙ ለማዳረስ፡ በምናደርገው ሓዋርያዊ ገድል፡ ይህ የኅዋ ሰሌዳ፡ እናንተን ለማገልገል፡ እጅግ አመቺና ቀልጣፋ ኾኖ እንደሚገኝ እናምናለን።
We have launched a new website which has much more functionality.
We wanted to make sure that our new website works better for those who use it. This involved gaining a better understanding of the different types of devices available - from desktop computers and tablets to mobile phones you might use to visit our site. The new website is a responsive, which means, it now displays at a suitable scale and resolution for each variation of device and browser.
Communicating with people to reveal the truth about ‘To reveal the truth about Ethiopia's entity as the Kingdom of God and Ethiopians' identity as the People of the Holy Covenant with God; and so, to safeguard and promote all that pertains to Ethiopia and Ethiopians.’ is the only theme which we purse on this website. We believe that our new website will help us and you to achieve this goal by making it easier for you to view, read, download, listen audio, watch videos etc...
We will continue to develop and improve other areas of the website, including a project section and pages which will allow us to translate contents onto different languages by working with volunteers involved. We will keep you informed about the progress of this work in due course.
We hope that this more user-friendly process will encourage more people to join, expanding the truth that ‘Ethiopia is the Kingdom of God and Ethiopians are the children of God’.
We are keen to hear your thoughts and suggestions on our new website and services.
N'bure-Id Ermias Kebede Wolde-Yesus, Ethiopia the Kingdom of God Servant.