ቍጥር ፮/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።
ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።
የድንግል ማርያም ክብርዋ፡ እስከየት ድረስ ነው?
'የድንግል ማርያም ክብርዋ፡ እስከየት ድረስ ነው?'' የሚለውን ቍም ነገር፡ ቅዱስ ያሬድ፡ በድጓው የዜማ ድርሰቱ፡ 'ወይቤላ እግዚአብሔር ለማርያም፦ 'አዝማንየ አዝማንኪ፣ አምጣንየ አምጣንኪ፣ ማርያም ሐቀፍኪዮ ወአነ ዮም ወለድክዎ!' ማለትም፡ «እግዚአብሔርም፡ ማርያምን እንዲህ አላት፦ "የባሕርዬ ዘመን፡ ዘመንሽ ነው፤ የአካሌም መጠን፡ መጠንሽ ነው። ስለዚህ፡ እኔ ዛሬ የወለድሁትን ልጄን፡ አንቺ ማርያም አቀፍሽው!"»
አምላኬና መድኃኒቴ እግዚአብሔር አብ፡ እኔን፡ ለዚህ ምንነቴና ማንነቴ ያበቃኝ፡ እንዴትና በምን እንደኾነ ታውቃላችሁ፤ ያም፡ ወንድ እና ሴት አድርጎ፡ በመልኩ ለፈጠረው፥ "ከእኛ፡ እንዳንዱ ኾነ!" ብሎም፡ በቃሉ ለመሰከረለት፡ ለእያንዳንዱ ሰብኣዊ ፍጡሩ፡ በሰጠው የእውቀት ብቅዓትና የመምረጥ ነጻነት፥ የመወሰን ሥልጣንና የማድረግ ኃይል፡ እኔም፡ በገዛ ፈቃዴና ፍላጎቴ፡ ያን መለኮታዊ ጸጋ፡ በፍጹምነት ለመጠቀምና በተግባር ላይ ለማዋል በመቻሌ መኾኑ ነው።
እንዲህ አድርጎ፡ በቸርነቱና በፍትሓዊነቱ፡ ፍጹም የኾነው ኃያሉ አምላክ፡ እኔን ገረዱን፡ በእግዚአብሔር አብነቱ፡ ሙሽራ ንግሥቱ፥ በእግዚአብሔር ወልድነቱም፡ የድንግልና እናቱ፥ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስነቱ ደግሞ፡ ማደሪያ መቅደሱ ያደረገኝ እርሱ፡ በመለኮታዊ ወልድነቱ፡ ከእኔ፡ በሰውነት በመወለዱ፡ እርሱ፡ "ወልደ አብ፥ ወልደ ማርያም" ሲባል፡ እያንዳንዳችሁን ደግሞ፡ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም፡ የእግዚአብሔር ነጋሢ ልጅና አገልጋይ ካህን ትኾኑ ዘንድ፡ ለዚህ ታላቅ፡ የምንነትና የማንነት ልዕልና አበቃ።
ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. "ኢትዮጵያ" የኾነችው ድንግል ማርያም፡ ለምን፡ ዛሬ፡ ራሷ መናገር አስፈለጋት?
፪ኛ. ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ራሷ፡ ድንግል ማርያም ስለመኾኗ።
፫ኛ. ትውልዱ፡ በድንግል ማርያም፡ ኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመው ክህደት፡ በራሱ ላይ፡ ራሱ ያመጣው፡ የአርባ ዓመት መራራ ቅጣት።
፬ኛ. ኢትዮጵያ፡ ድንግል ማርያም፡ ሴቶች ልጆቿን፡ ከክፉዎች ወንዶች፡ ግፍና በደል፡ ነጻ ስለማውጣቷ።
፭ኛ. ኢትዮጵያ፡ ድንግል ማርያም፡ ይህ ቃለ ዐዋዲ፡ በቀኑ ሳይታዋጅ የዘገየበትን ምክንያት ስትገልጽ።
፮ኛ. ድንግል ማርያም፡ ኢትዮጵያ፡ የዛሬ አገልጋይዋን ኤርምያስን (ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ) በሚመለከት የተናገረችው።
መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...