ኪዳናዊ አክሊለ-ጊዮርጊስ፡ ስለትክክለኛውና ስለእውነተኛው የምድር ቅርጽ በተመለከተ ለላከልን የእ-ጦማር ጥያቄ፡ የተሰጠ መልስ።
Submitted by etkog12 on Sat, 03/26/2016 - 11:41ከኪዳናዊ አክሊለ-ጊዮርጊስ፡ የደረሰን እጦማር፦
+ዮም ፍሥሓ ኮነ!
በእንተ ፍልሰታ፡ ውስተ አርያም!
ለእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያም!+
ጤናውን ይስጥልኝ፣ በእግዚኣብሔር መንግሥት፣ ኪዳናውያትና ኪዳናውያን እኅቶቼና ወንድሞቼ! እንደምን ኣላችሁልኝ!?
ቤተሰቤና እኔ፣ በቸሩ ፈጣሪ እርዳታ፣ በፍጹም መልካም ሕይወት እንገኛለን፤ ምስጋናችሁ ዛሬም ይድረሳቸውና።
በዚህች እ-ጦማሬ ላስተላልፍ የፈለግኁትን ኣስተያየትና የሃሳብ ጥቆማ- የኪዳናዊ ጋሽዬ ኤርሚያስ ከበደ ቃለ መጠይቅ ሥዕላዊ መጽሔትን በተመለከተ- ሥዕላዊ መጽሔቱን ስመለከት፡ ገና ከመነሻው ላይ በተመለከትኩት፣ እንደእኔ እምነት ግን ትክክለኛ ኣይደለም ብዬ በያዝኩት፣ የምንኖርባትን ዓለም ሥዕላዊ መግለጫ ወይም የቅርፅና ሕልውና ጉዳያን በተመለከተ ነው።