የ፳፻፲፩ ዓመተ-ምሕረት፡ የአዲስ ዓመት መልእክት።
Submitted by etkog12 on Mon, 09/10/2018 - 17:08ርእሰ አንቀጽ
እግዚአብሔርን፥ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ልጆች በሚመለከት፡ በብሉዩ ኪዳን ነቢይ፦"እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ-ዓለም፤ ወገብረ መድኃኒተ፡ በማእከለ ምድር፤ አንተ አጽናዕካ፡ ለባሕር በኃይልከ፤ ወአንተ ሰበርከ ርእሰ-ከይሲ፡ በውስተ ማይ፤ ወአንተ ቀጥቀጥከ፡ አርእስቲሁ ለከይሲ። ወወሀብኮሙ ሲሳዮሙ፡ ለሕዝበ-ኢትዮጵያ!
"ዓለሙን ከመፍጠርህ በፊትም ኾነ፡ በኋላ፡ ምንጊዜም፡ ንጉሣቸው የኾንከውና በምድር መካከል፡ መድኃኒትን [በኢትዮጵያዋ ድንግል ማርያም] ያደረግህ፥ ባሕርንም፡ በኃይልህ [በኢትዮጵያው ኢየሱስ መሲሕ] ያጸናህ፥ [በእርሱ፡ በሰላምህ]፡ የእባቡን ጭንቅላት፡ በውኃ ውስጥ የሰበርህ፥ የዘንዶውንም ራሶች የቀጠቀጥህ፡ አንተ እግዚአብሔር፡ የቅዱሱ ኪዳን ሕዝብህ፥ የቅድስት እናትህ፡ የድንግል ማርያምምልጆች ለኾኑት፡ ለኢትዮጵያ ሰዎች፡ የሚያስፈልጋቸውን ሲሳይ [ምግብን፣ ልብስን፣ መኖሪያን] ኹሉ ሰጠሃቸው!" ተብሎ የተነገረ የትንቢት ቃል መኖሩ ይታወቃል።