በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የፌስቡክ መድረክ፡ ለቀረቡ ጥያቄዎችና ትችቶች፡ የተሰጠ ምላሽ።

፩ኛ. ከኢእመ የፌስቡክ መድረክ የተሰጠ፦

የቅዱስ ያሬድ ሥዕል አጭር ማብራሪያ።

     ስመ-ጥሩው፡ ኢትዮጵያዊ የዜማ ደራሲና ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡ በመንፈስ ቅዱስ ተመሥጦ፡ የደረሰውን የምስጋና ድርሰት ያዜመው፡ መላእክት፡ በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ሥላሴነት ለሚመለከው ፈጣሪያቸው፡ ለእግዚአብሔር፡ በዚሁ የሥላሴ ምሥጢር፡ በሰማያት በሚያቀርቡትና አጥንትን በሚያለመልመው፡ "ግእዝ፥ ዕዝልና አራራይ" በተባሉት የዜማ ስልቶች ነው። ልዩ ጣዕም ካለው፡ ከዚህ የላሕይ ድምፁ የተነሣ፡ ቅዱስ ያሬድን፡ ማኅሌታዊ ድርሰቱን ሲያዜም የሚያደምጠው ኹሉ፡ በዚያው በመንፈስ ቅዱስ የመመሰጥ ዕድል ፈንታን ያገኛል።

     በቅዱስ ያሬድ ዘመን፡ ኢትዮጵያን ያስተዳድር የነበረው ዕድለኛ የዘውድ መሪ፡ የገናናው፡ የአጼ ካሌብ ልጅ፡ አጼ ገብረ-መስቀል ነበር። ማኅሌታዊው ካህን፡ ድርሰቱን በሚያዜምበት ጊዜ፡ እርሱም፡ እንደቅዱስ ያሬድ፡ በመንፈስ ቅዱስ፡ እጅግ ይመሰጥ ነበር። ከሥነ በዓላቱ በአንደኛው ላይ፡ ቅዱስ ያሬድ፡ ማኅሌታዊ ድርሰቱን እያስሰማ፡ በሚያዜምበት ጊዜ፡ ሳይታወቀው፡ ወደዚሁ አጼ ዙፋን ቀርቦ ኖሮ፡ ኹለቱም፡ በማኅሌቱ ድርሰትና ዜማ፡ በጽኑ በመመሰጣቸው፡ አጼውም፡ ሳያውቅ፡ የጦሩን ጫፍ፡ በካህኑ ያሬድ እግር ላይ አሣርፎ ሲወጋው፥ ማኅሌታዊውም፡ መወጋቱ ሳይሰማው፡ ዜማውን ዝም ብሎ መቀጠሉ ሲነገር የሚኖር ዜና ነው።

     ይህ ሥዕል የሚያዘክረው እውነታ፡ ያን ትንግርታዊ ኹኔታ ነው።

ሥዕሉን ለመመልከት!... 

የጥያቄና መልሱን ሙሉ ክንውን፡ በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...