ቅዱስ ያሬድ

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የፌስቡክ መድረክ፡ ለቀረቡ ጥያቄዎችና ትችቶች፡ የተሰጠ ምላሽ።

፩ኛ. ከኢእመ የፌስቡክ መድረክ የተሰጠ፦

የቅዱስ ያሬድ ሥዕል አጭር ማብራሪያ።

     ስመ-ጥሩው፡ ኢትዮጵያዊ የዜማ ደራሲና ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡ በመንፈስ ቅዱስ ተመሥጦ፡ የደረሰውን የምስጋና ድርሰት ያዜመው፡ መላእክት፡ በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ሥላሴነት ለሚመለከው ፈጣሪያቸው፡ ለእግዚአብሔር፡ በዚሁ የሥላሴ ምሥጢር፡ በሰማያት በሚያቀርቡትና አጥንትን በሚያለመልመው፡ "ግእዝ፥ ዕዝልና አራራይ" በተባሉት የዜማ ስልቶች ነው። ልዩ ጣዕም ካለው፡ ከዚህ የላሕይ ድምፁ የተነሣ፡ ቅዱስ ያሬድን፡ ማኅሌታዊ ድርሰቱን ሲያዜም የሚያደምጠው ኹሉ፡ በዚያው በመንፈስ ቅዱስ የመመሰጥ ዕድል ፈንታን ያገኛል።