ከኪዳናዊ ኃይለ ማርያም፡ የደረሰን እጦማርና ለዚያ እጦማር የተሰጠ ምላሽ።

ከኪዳናዊ ኃይለ-ማርያም የተላከ እጦማር፦

ተፈጸመ ትስብእት፡ በኢትዮጵያ ማርያም ድንግል!
በብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል፡ ዜናዌ ቃል!

የተወደድህና የተከበርህ ኪዳናዊ ወንድሜና ክህነታዊ ባልደረባዬ ጋሽዬ! 
    እንደምንድር ሰንብተሃል? ይመስገነው! እኔ፡ ደኅና ነኝ።
    በዮሓንስ ራእይ፡ ሔኖክንና ኤልያስን የመሰሉ፥ በእነርሱም መንፈስ የተገለጹ፥ "ኹለቱ ምስክሮቼ፥ ኹለቱ ወይራዎችና ኹለቱ መቅረዞች" ያላቸው፡ «በፍጻሜ ዘመን የተገለጹት፡ በቤተ መቅደስ የተሠዋው፡ የበራክዩ ልጅ፡ ''ካህኑ ዘካርያስ''ና በኤልያስ መንፈስ የተገለጠው፡ የዘካርያስ ልጅ፡ ''መጥምቁ ዮሓንስ'' ናቸው።» ብለን፡ መደምደም ይቻለን ይኾን? ወይስ፡ መንፈስ ቅዱስ የሚያውቃቸውና የመረጣቸው፡ ኹለቱ ምስክሮቼ፥ ኹለቱ ወይራዎችና ኹለቱ መቅረዞች ያላቸው፡ ቅዱሳትና ቅዱሳን፡ «እርሱ፡ መንፈስ ቅዱስ ባወቀና በወደደ ጊዜ ይገለጣሉ!»  በሚለው እንጽና? ማለትም፡ በእኛ፡ በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያትና ኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ «የሚጠበቁ ቅዱሳትና ቅዱሳን የሉም!» የሚለው፡ ቃለ ሃይማኖት፡ እንደተጠበቀ ኾኖ ማለት ነው። 
አክባሪህና የአገልግሎት ባልደረባህ፦ ኃይለ-ማርያም።

ከኢእመ፡ የተሰጠ ምላሽ፦