''ዕለት የሚቀየረው፡ በስንተኛው ሰዓት ነው?'' ተብሎ ለቀረበ ጥያቄ፡ የተሰጠ መልስ።
Submitted by etkog12 on Mon, 09/28/2015 - 03:42
ከ"ሰው ኾኖ መገኘት"፡ የቀረበ ጥያቄ ፦
ቀን የሚቀየረው በስንተኛው ሰዓት ነው? ብዙ ሰባኪዎች ቀን የሚቀየረው ጠዋት ነው ይላሉ፡፡ እርሶ መጽሐፍ ላይ እኩለ ሌሊት ነው የሚቀየረው የሚል አንብቤ ነበር፡ ፡ ይህ ልዩነት ለምን እንደተከሰተ ቢያብራሩልኝ፡፡ አመሰግናለሁ
ከኢእመ የተሰጠ መልስ፦
ስለጥያቄዎ፡ እግዜር ይስጥልኝ! መልሳችንም፡ ባⶽር፡ እንደሚከተለው ነው፦
፩. አዎን! ዕለት (ቀን) የሚቀየረው፡ ከእኩለ ሌሊት፥ ማለትም፡ ከጨለማው ፮ኛ (ስድስተኛ)፥ ወይም፡ ከዕለቲቷ ፳፬ኛ (ሃያ አራተኛ) ሰዓት በኋላ ባለችው ቅጽበት ነው፤ ምክንያቱም፡ መሬት፡ በፀሓይ ዙርያ የምታደርገው፡ የ፩ (አንድ) ዕለት፥ ማለትም፡ የ፳፬ (ሃያ አራት) ሰዓታት፥ ወይም፡ የ፷ (ስድሳ) ኬክሮስ ዑደት አብቅቶ፡ የአዲሱ ዕለት ዑደት፡ ፩ ኬክሮስ፥ ወይም፡ ፩ ሰዓት ተብሎ የሚጀመርበት፡ የጊዜ ቀመር (አቈጣጠር) መነሻ፡ በዚያች በእኩለ ሌሊቷ አፍታ ላይ ስለኾነ ነው።
መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...