ዓቢይ ጾም - ሑዳዴ።

የ፳፻፲፩ዱ (የሃያ መቶ ዐሥራ አንዱ=የኹለት ሺ ዐሥራ አንዱ) ዓመተ-ምሕረት ዓቢይ ጾም።

ይኸውም፡

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፥ 
በፍጥረታተ-ዓለማቷም ላይ ሊፈጽም፡

የክፋትና የሓሰት፥ የጥፋትና የሞት አባት የኾነው ዲያብሎስ፡ ከነጭፍሮቹ፡ አሢሮ የቀፈቀፈውንና
ሲያካኼድ የኖረውን፥ አኹንም እያካኼደ ያለውን፡
የመንፈስና የነፍስ፥ የሥጋና የኹለንተና ጦርነት፡

ኢትዮጵያዊው የዘለዓለሙ አጼ፡ ኢየሱስ መሲሕ፡
ከኢትዮጵያ አጼዪት እናቱ፡ ከእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም በተወለደበት ሰውነቱ፡
ለአንዴና ለመቼውም ጊዜ፡ ሊያስወግድ፡ በእግዚአብሔር በግነቱ፡ ለፍጥረቱ ቤዛ ኾኖ ወደሚታረድበት፡
ወደተጋድሎው የሰልፍ መስቀለ-ሞቱ አደባባይ ይደርስ ዘንድ፥ 
በዚያም፡ በደም በታለለ የእሾህ አክሊሉ አማካይነት፡ 
በትንሣኤው፡ አንበሳዊ ኃይሉም፡ ድል አድራጊነት፡ የሰላም ዘውዱን ይቀዳጅ ዘንድ፣ 
ለእኛም፡ ለኢትዮጵያ ልጆቹ፡ ያቀዳጀን ዘንድ፡
እንደፀሓይ የማለዳ ጎሕ፡ ከሙሽርነት አዳራሹ ወጥቶ፡
የዐርበኝነት ጕዞውን የጀመረበት ጊዜ፡ ዓመታዊ መታሰቢያ።

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...