ዓቢይ ጾም፥ ሑዳዴ፥ ታላቁ ጾም፥ ሕዝባዊ ጾም፥ ምጽዋት፥ ስግደት። የካቲት ፲ ቀን፥ ፳፻፲ ዓ.ም. (17 February 2019).

ወቅታዊ መልእክት፣ ለኢትዮጵያ ልጆች።

በእግዚአብሔር ስም፡ ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን እያቀረብንላችኹ፣
''ግበሩኬ! እንከ ፍሬ ሠናየ፡ ዘይደልወክሙ ለንስሐ!''፥ ማለትም፡ ''እንግዲህስ! ለንስሐ የሚያበቃችኹን፡ በጎ ሥራ ሥሩ!'' በሚለው፡ የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፡ ከታች የሠፈሩትን መልእክቶች፡ በጥሞና እንድትከታተሏቸው እናሳስባለን። ማቴ. ፫፥ ፰።

ዓቢይ ጾም - ሑዳዴ።

የ፳፻፲፩ዱ (የሃያ መቶ ዐሥራ አንዱ=የኹለት ሺ ዐሥራ አንዱ) ዓመተ-ምሕረት ዓቢይ ጾም።

ይኸውም፡

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ፥ 
በፍጥረታተ-ዓለማቷም ላይ ሊፈጽም፡

የክፋትና የሓሰት፥ የጥፋትና የሞት አባት የኾነው ዲያብሎስ፡ ከነጭፍሮቹ፡ አሢሮ የቀፈቀፈውንና
ሲያካኼድ የኖረውን፥ አኹንም እያካኼደ ያለውን፡
የመንፈስና የነፍስ፥ የሥጋና የኹለንተና ጦርነት፡