ሔዋን

የዘለዓለማዊቷ እመቤታችንን፡ የቅድስት ድንግል ማርያምን እውነተኛ ምንነትና ማንነት በሚመለከት፡ ከኪዳናውያን፡ ለኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የተላከ መልእክት።

የዘለዓለማዊቷ እመቤታችንን፡ የቅድስት ድንግል ማርያምን እውነተኛ ምንነትና ማንነት በሚመለከት፡ ኹለት፡ ኪዳናውያን፡ የኢትዮጵያ ልጆች፡ በደብዳቤ ያደረጉትን የአስተያየት ልውውጥ፡ በእጦማር ስለተላከልን፥ እኛም፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም፡ በዚህ የእውቀት ገበታ ላይ፡ የበኩላችንን፡ ተጨማሪ ማብራሪያ አክለንበት፡ ለብዙዎች፡ የእውቀታቸውን አድማስ እንደሚያሰፋላቸው በማመን፡ በኅዋ አውታር መድረኮቻችን ኹሉ ላይ፡ እንደሚተለው አቀናብረን አቅርበንላችኋል።